አሜሪካ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት በኮንግረስ ንግግር ስያደርጉ ከዴሞክራቶች ከፍተኛ ተቃውሚ ገጠማቸው፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/06/2018፡- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኮንግረስ ባደረጉት ንግግር የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታሪፎችን ውድቅ ማድረጉንም ከማውገዝ እስከ የኢራኑ ኒውዩክሌር እና በስልጣን ቆይታቸው አስቀራኃቸው ያሉዋቸውን ጦርነተቶች ዘርዝረዋል፡፡

ትራምፕ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ እንደገለፁት “ስምንት ጦርነቶች” እንዲቆሙ ማድረጋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከልም “የኢትዮጵያ እና የግብፅ” ይገኝበታል ብለዋል።

በታሪክ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ካደረጓቸው ንግግሮች ረዥሙ ተብሎ የተመዘገበው የትራምፕ ንግግር 1 ሰዓት ከ29 ደቂቃ ሲሆን መንግሥታቸው ሕገ ወጥ ስደትን በመቀነስ እና ደቡባዊ የአገሪቱን ድንበር በማስጠበቅ ውጤታማ ስራ መስራቱን ገልፀዋል።

ሪፐብሊካኖች የትራምፕን ንግግር በጭብጨባ ሲደግፉ ዴሞክራቶችም የትራም ንግግርን በሚያቋርጥ መንገድ ተቃውሞታል፡፡

የቴክሳሱ ዴሞክራት የሕዝብ እንደራሴ አል ግሪን “ጥቁሮች ዝንጀሮ አይደሉም” የሚል ጽሑፍ ከፍ አድርገው በማሳየታቸው ከአዳራሹ እንዲወጡ ተደርጓል።

ትራምፕ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማን ዝንጀሮ አድርጎ የሚያሳይ ቪድዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ከለጠፉ በኋላ ማጥፋታቸው ይታወሳል።

የሜኒሶታ ዴሞክራት የሕዝብ እንደራሴ ኢልሐን ኦማር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ትራምፕን “ውሸታም” ብለው ሲሳደቡ ተስምተዋል።

የቨርጂኒያ አገረ ገዢ አቢጌል ስፓንበርገር በበኩላቸው ስደተኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ “ቤተሰብን የሚበትን ነው” ሲሉ አጣጥለዋል።

ትራምፕ ሌላው ያነሱት የኢራንን ጉዳይ ሲሆን ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት እንደማይፈቅዱ በድጋሚ ተናግረዋል።

ትራምፕ “የእኔ ምርጫ ችግሩን በዲፕሎማሲ መፍታት ነው። አንድ ጉዳይ ግን እርግጥ ነው። እሱም፤ የዓለም ቁጥር አንድ የሽብር ደጋፊ የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት አልፈቅድም” ብለዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates