መካከለኛ ምስራቅ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዳግመኛ ኢራንን አስጠነቀቁ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/06/2018፡- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻለች “በጣም ከባድ የሆነ መዘዝ” ሊገጥማት እንደሚችል በመግለጽ በድጋሚ አስጠነቀቁ።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ከሥምምነት ላይ መድረስ አለባቸው ካሉ በኋላ ይህንንም በሚቀጥለው ወር ማድረግ ይቻላል ብለዋል።
አክለውም ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ ግን ወደ ሁለተኛው ዙር እርምጃ እንደሚገቡ እና ያም ለኢራን “በጣም ከባድ” እንደሚሆን ተናግረዋል።
ትራምፕ ለመገናኛ ብዙኃን ሲናገሩ ስምምነት የመድረስ አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል።
“ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው፤ ይህ ካልሆነ ግን ሁኔታው ​​​​በጣም የከፋ ሊሆን ይችላል።
ምንም ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ፣ የኢራን ሁኔታ በጣም ከባድ እና በጣም የከፋ ይሆናል” ብለዋል።
“ከስምምነት ላይ መድረስ አለብን፤ አለበለዚያ ሁኔታዎች የበለጠ ይካረራሉ እና አስቸጋሪ ይሆናሉ” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ድርድሩ እንዲቋረጥ ጠይቀዋቸው እንደሆን ተጠይቀው “እንደዚያ አልተነጋገርንም። የምፈልግ ከሆነ ግን አነጋግራቸዋለሁ” ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ኢራናውያን “መጀመርያ ላይ መስማማት ነበረባቸው ያንን ማድረግ ስላልቻሉ ወደ ዘመቻ ‘ሚድናይት ሀመር’ ገባን። አሁን ከስምምነት ላይ የማይደርሱ ከሆነ ለኢራን እጅግ ከባድ ይሆናል።”
ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ ዳግም ድርድር የጀመሩት ባለፈው ሳምንት አርብ በኦማን ዋና ከተማ መስካት ነበር።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates