የአሜሪካ ጦር በሶሪያ ካለው ቁልፍ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ጠቅልሎ መውጣቱ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/06/2018፡- የአሜሪካ ጦር ሐሙስ ዕለት ከሶሪያ ወሳኝ አል ታንፍ ከተባለው ወታደራዊ ካምፕ ጠቅልሎ መውጣቱን አስታወቀ።
የአሜሪካ ጦር ለቅቆ የወጣው ወታደራዊ ካምፕን ለሶሪያ ጦር ማስረከቡን አስታውቋል።
አሜሪካ እና ሶሪያ በቅርቡ የሁለቱን አገራት ወታደራዊ ትብብር የሚያጠናክር ስምምነት ፈርመው ነበር።
አል ታንፍ ወታደራዊ ጦር ሰፈር በሶሪያ፣ በዮርዳኖስ እና በኢራቅ ድንበር አካባቢ የሚገኝ ነበር።
ወታደራዊ ጦር ሰፈሩ የተመሠረተው በአውሮፓውያኑ 2014 ሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ላይ በነበረችበት ወቅት ነበር።
አሜሪካ በኢስላሚክ ስቴት ታጣቂዎች ላይ ለምትፈጽመው ጥቃት ይህ የጦር ካምፕ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው ተብሏል።
የእስላሚክ ስቴት በአንድ ወቅት ሰፊ የኢራቅ እና የሶሪያ አካባቢዎችን ይቆጣጠር የነበረ ሲሆን፣ በአውሮፓውያኑ 2019 ተሸንፏል።
ከዚያ በኋላ ግን የጦር ሰፈሩ የሚገኘው ደማስቆ እና ቴህራንን በሚያገናኘው መንገድ አቅራቢያ በመሆኑ አሜሪካ ከኢራን ጋር ላላት ፍጥጫ ስትራቴጂክ ስፍራ በመሆን እያገለገለ ነበር።
ዋሺንግተን ጦር ሰፈሩን ይዛ መቆየት ፈልጋ የነበረ ቢሆንም፤ የሶሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባሽር አል አሳድ በ2024 መጨረሻ ላይ ከሥልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ውሳኔዋን ዳግም አጢናዋለች።
የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር የጦር ካምፑን መረከቡን ይፋ አድርጓል።



