ኢትዮጵያ
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ ሰጠ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/06/2018፡- የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ እንግዶችን ለማስተናገድ የላቀ ዝግጅት ማድረጓ መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።
የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫና የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ መሪዎችንና የልዑካን ቡድኖችን ተቀብላ በአግባቡ ለማስተናገድ ከምንጊዜውም በላይ የተሟላ ዝግጅት ማድረጓን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተስፋሁን ጎበዛይ በሰጡት መግለጫ፤ ከአፍሪካ ኅብረት 39ኛው የመሪዎች ጉባዔ ጋር በተያያዘ በሚደረጉ ስብሰባዎች ከ17 ሺህ በላይ የልዑካን ቡድን አባላት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ብለዋል።
ከ800 በላይ የሚዲያ ባለሙያዎችም ጉባዔዎቹን ለመዘገብ ፈቃድ መጠየቃቸውን በመግለጫቸው አንስተዋል።
ኢትዮጵያ እንደ አስተናጋጅ ሀገር ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ መሪዎች፣ ልዑክና እንግዶችን ተቀብላ ከማስተናገድ ባሻገር በርካታ የሁለትዮሽ ውይይቶችን ለማድረግ ዝግጁ ናት ሲሉም ገልጸዋል።
አክለውም፥ የኅብረቱ መቀመጫና የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባም በአኅጉሩና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች መሪዎችንና የልዑካን ቡድኖችን ተቀብላ ለማስተናገድ ከምንጊዜውም በላይ የተሟላ ዝግጅት አድርጋለች ብለዋል።



