
ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/05/2018፡- የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ ረቡዕ ዕለት ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር በባህር ትብብር እና ሱዳን ወደ አፍሪካ ህብረት የመመለስበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት መገናኘራቸው የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
እንደ ሱና ዘገባ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢድሪስ ከሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ፀሐፊ ሙዓዊያ ኦስማን ካሊድ እና ከምክትል የስለላ ዳይሬክተር አባስ ሞሃመድ ባኪት ጋር በመሆን ሱዳን በወደብ አስተዳደር እና በሁለትዮሽ ኮሚቴዎች እንቅስቃሴ ላይ የቴክኒክ ትብብር እንደምትፈልግ ለጅቡቲ መንግስት ጥይቀዋል፡፡
“መንግስት ከጅቡቲ ጋር በመተባበር፣ በወደብ ዘርፍ እውቀትን በመለዋወጥ እና የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ላይ ፍላጎት አለው” ማለታቸው ሱና ዘግበዋል።
ጥቅምት 2021 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመ በኋላ የአፍሪካ ህብረት የሱዳንን አባልነት አግዶ የሲቪል አገዛዝን ወደነበረበት መመለስ እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።
ሆኖም ወታደራዊ ሐይሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ኢድሪስ የሚመራ የሲቪል መንግስት ቢመሰርትም፣ ሰራዊቱ በአስፈፃሚ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳለው ይነገራል።
ጅቡቲ በአሁኑ ጊዜ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የ39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ ጉባኤ እና ከየካቲት 11-15 በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሊቀመንበርነት ትመረዋለች። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢድሪስ ሱዳን ወደ ሕብረቱ የመመለስ ፍላጎት እንዳላት ለጅቡቲ ጥያቄ ያቀረቡት፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሱዳን ወደ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) የመመለስ ፍላጎት እንዳላተት እየተገለፀ ነው፡፡
ኢድሪስ ከማንኛውም የፖለቲካ ሂደት በፊት የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ከከተማ ማዕከላት እንዲወጡ እና ትጥቅ እንዲፈቱ የሚያስገድድ የመንግስት የሰላም ተነሳሽነት ማቅረባቸው ዘግባው አመልክተዋ።
ፕሬዝዳንት ግሌ ጅቡቲ ለሱዳን ሉዓላዊነት እና ለግዛት አንድነት ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ገልጸው የሰላም ተነሳሽነቶችን ለመደገፍ ፈቃደኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ነገር ግን በተለያዩ የሽምግልና ሂደቶች መካከል የበለጠ ቅንጅት እንደሚያስፈልግ አፅንዖት መስጠታቸው ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ጎን ለጎን ኢድሪስ ከጅቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ካሚል መሐመድ ጋር ተገናኝተው የዶራሌህ ባለብዙ ዓላማ ወደብ መጎብኘታቸው ተገልፀዋል።



