አሜሪካ

ትራምፕ ባወጡት መመሪያ መሰረት ከ75 ሀገራት ለሚመጡ የአሜሪካ ዜጎች ቤተሰቦች ከዛሬ ረቡዕ ጥር 13 ጀምሮ የቪዛ ክልከላ ተግባራዊ ሆኗል::

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/05/2018፡- ዛሬ ረቡዕ፣ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እንደ “ጥቁር ረቡዕ” ሊመዘገብ የሚችል ቀን ነው የሚሉት ተንታኞች ከዋይት ሃውስ የወጣው አዲሱ አዋጅ ተግባራዊ መሆን በጀመረባቸው ጥቂት ሰዓታት ውስጥ፣ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች ከፍተኛ የሆነ ትርምስ ተፈጥሯል።

75 ሀገራትን ኢላማ ያደረገው እና የአሜሪካ ዜጎችን የትዳር አጋሮች፣ ወላጆች እና ልጆች ሳይቀር “ቪዛ አትሰጡ” በሚል ያገደው ይህ ውሳኔ፤ አሜሪካ ለ60 ዓመታት ያህል ስትከተለው የነበረውን “የቤተሰብ አንድነት” መርህ ይንዳል ተብለዋል።

ይሄ በ75 ሀገራት ላይ የታወጀውን የጉዞ እገዳ ተከትሎ ከዛሬ ጥር 13 ቀን ጀምሮ ሁሉም የኢሚግራንት ቪዛዎች፣ የአሜሪካ ዜጋ ልጆች፣ የትዳር አጋሮች እና ወላጆች ጭምር ወደ አሜሪካ ለመምጣት ቪዛ አይሰጣቸውም ተብለዋል።

ይሄ እገዳ ከሁሉም በላይ የአሜሪካ ዜጎችን ከሚስቶቻቸው፣ ልጆቻቸው እና ወላጆቻቸው የሚነጥል አደገኛ ውሳኔ ነው በማለት ብዙዎች እየተቃወሙት ይገኛሉ፡፡

አወዛጋቢ ውሳኔዎች በመወሰን የሚታወቁት ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ ፈረስት የሚል አቋም ያላቸው ሲሆን ይህ ውሳኔ ደግሞ እነዚህ ቪዛ የተከለከሉ ሰዎች በአሜሪካ ኢኮኖሚ ብዝበዛ እንደማያስከትሉ እስኪረጋገጥ ድረስ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates