አሜሪካ

የትራምፕ አስተዳደር ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳንን ጨምሮ የ19 አገራት ዜጎችን የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሊመረምር ነው ተባለ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/03/2018፡-  የትራምፕ አስተዳደር ኤርትራን ጨምሮ ከ19 አገራት ወደ አሜሪካ የገቡ በሁሉም ዜጎች የመኖሪያ እና የሥራ ፈቃድ ላይ እንደገና ምርመራ ሊያደርግ እንደሆነ ተገልጿል።

የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት ኃላፊ ጆሴፍ ኤድሎው እንዳሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ “አሳሳቢ ከሆኑ አገራት የመጡ ስደተኞች በሙሉ የእያንዳንዳቸው የመኖሪያ እና የሥራ ፈቃድ፣ በጥብቅ እንደገና እንዲመረምር” መመሪያ ሰጥተዋል።

ቢቢሲ እነዚህ አገራት እነማንን እንደሚያካትት ሲጠይቅ በሰኔ ወር ያወጣውን አዋጅ ተጠቅሷል። እነዚህም አገራት ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ አፍጋኒስታን፣ የመን፣ ኩባ፣ ሄይቲ፣ ኢራን፣ ቬንዙዌላን እና ታርሚክስታን እንደሚያካትት ተብራርቷል።

ይህ ትዕዛዝ የተሰማው አንድ አፍጋኒስታናዊ ረቡዕ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ሁለት የብሔራዊ ዘብ አባላት ላይ ተኩሶ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ነው። ጥቃት ከደረሰባቸው የፀጥታ አባላት አንዷ እንደሞተች እየተገለፀ ይገኛል።

እናም ረቡዕ ዕለት በአሜሪካ ጦር አባላት ላይ የተፈፀመው ጥቃት ትራምፕ ጠንካራ ምላሽ እንዲሰጡ አድርጓቸዋል እየተባለ ነው። “ይህ ጥቃት በአገራችን ላይ የተጋረጠውን ትልቁን የብሔራዊ ደኅንነት ስጋት አጉልቶ ያሳያል” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates