አሜሪካ

አሜሪካ ባቀረበችው የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ላይ በሚደረገው ንግግር “ከፍተኛ መሻሻል” መታየቱ ተገለጸ።

ኢትዮሞኒር፡ 15/03/2018፡- አሜሪካ፤ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነትን ለመቋጨት ያቀረበችውን የሰላም ዕቅድ በተመለከተ የሚደረገው ንግግር ላይ “ከፍተኛ መሻሻል” መታየቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ተናገሩ።

ሩቢዮ፤ የዩክሬን እና አውሮፓ ተደራዳሪዎች በሲውዘርላድ ጄኒቫ ከተማ ካደረጉት ስብሰባ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ነገር ግን “አሁንም፤ መከናወን ያለበት የተወሰነ ስራ አለ” ብለዋል።

በአሜሪካ የተዘጋጀው እና ለሩሲያ ያደላ ተደርጎ የታየው የሰላም ስምምነት ዕቅድ ሾልኮ ከወጣ በኋላ ዩክሬን እና አውሮፓውያን አጋሮቿ ስጋታቸውን አሰምተዋል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ ዕቅዱ ለሰላም ስምምነት “መሠረት” እንደሚሆን ተናግሮ ነበር።

ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ፤ ዩክሬን “እጅግ ከባድ ምርጫን ልትጋፈጥ ትችላለች፤ ክብርን ማጣት ወይም ቁልፍ አጋርን የማጣት አደጋ ያጋጥማታል” በማለት እቅዱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ሲገልጹ ተደምጠዋል።

ሩቢዮ፤ እሁድ ምሽት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በጄኔቫ የሚገኙት ተደራዳሪ ቡድኖች “በጣም ጥሩ ቀን” እንዳሳለፉ ተናግረዋል።

የንግግሩ ዋነኛ ዓላማ፤ 28 ነጥቦችን በያዘው የአሜሪካ የሰላም ዕቅድ ላይ የሚገኙ “ክፍት ጉዳዮችን” ለማጥበብ መሞከር እንደሆነ አስረድተዋል።

በንግግሩ የተሳተፉ አካላትም ይህንን ግብ “ተጨባጭ በሆነ መልኩ” ማሳካታቸውን አስታውቀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates