አሜሪካ

አሜሪካ ወደ ሃገሯ የሚገቡ ተጓዦች የ15 ሺ ዶላር ቦንድ እንዲያሲዙ የሚያስገድድ ፖሊሲ ልትተገብር መሆኑ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/11/2017፡ አሜሪካ ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ መተግበር የሚጀምር አዲስ የቪዛ ፖሊሲ ይፋ አድርጋለች።

ይህ ፖሊሲ እንደ አውሮፓዉያኑ አቆጣጠር ከነሃሴ ሃያ ጀምሮ በቱሪስትና ቢዝነስ ቪዛ ወደ ሃገሪቷ የሚገቡ ተጓዦች አስራ አምስት ሺ ዶላር እንዲያስይዙ የሚያስገድድ ሲሆን፤ አላማውም በጊዚያዊ ቪዛ ገብተው ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ የሚቆዩ መንገደኞችን ለመቀነስ ነው ተብሏል።

ተጓዦች ቪዛ በተመታላቸው ሰላሳ ቀናት ውስጥ የሚጓዙ ከሆነ፣ በተፈቀደላቸው መግቢያና መውጫ ኤርፖርት የሚገቡና የሚወጡ ከሆነ፣ እንዲሁም ቪዛው ሳይቃጠል ሃገሪቱን ለቀው የሚወጡ ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ እንደሚመለስ ተገልጿል።

ፖሊሲው በጊዚያዊ ቪዛ ገብተው የሚከርሙ ዜጎች  በሚበዙባቸው ሃገራት ለሙከራ የሚተገበር ሲሆን፤ እነኝህ ሃገራት የትኞቹ እንደሆኑ በይፋ አልተገለፀም።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates