ማህበራዊ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ከተሞች የሚያደርጋቸው በረራዎች መሰረዛቸው ተሰማ፡፡

የበረራዎቹን መቋረጥን በተለመከተ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ምክንያትም ሆነ መግለጫ የለም።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/05/2018፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች አየር ማረፊያዎች የሚያደርጋቸው በረራዎች መሰረዛቸው ተነገረ።

ቢቢሲ ትግርኛ ዛሬ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች መቋረጣቸውን ከተጓዦች እና ከክልሉ አንድ ኃላፊ ማረጋገጡ ዘግበዋል።

ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ ትኬት ቆርጠው የነበሩ መንገደኞች የሐሙስ ጥር 21/2018 ዓ.ም. መሰረዛቸውን የሚያስታውቅ አጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደደረሳቸው ተናግረዋል።

በመልዕክቱ ላይ “ከዕቅድ ውጪ በመሆነ ምክንያት” በረራው መሰረዙን እና መንገደኞች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወይም የጉዞ ወኪላቸውን እንዲያገኙ መክሯል።

ነገር ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራዎቹን መቋረጥን በተለመከተ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ምክንያትም ሆነ መግለጫ የለም።

ስለ በረራዎች መሰረዝ የተጠየቁት የክልሉ ትራንስፖርት ኃላፊ አቶ ታደለ መንግሥቱ በረራዎች መቋረጣቸውን አረጋግጠው፤ ነገር ግን ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

 

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የአየር መንገዱ ኃላፊም ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች መቋረጣቸውን አረጋግጠዋል።

እኚሁ የአየር መንገዱ ባልደረባ እንደገለጹት “በረራዎች ለዛሬ [ሐሙስ] ብቻ ነው የተሰረዙት፤ ነገር ግን የቀጣይ ቀናት በረራዎች በሚኖረው ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል” በማለት ለውሳኔው ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

በዚህም ምክንያት ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ፣ አክሱም፣ ሽሬ እና ሑመራ ከተሞች ሐሙስ ዕለት የሚደረጉ በረራዎች እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች መሰረዛቸው ተሰምቷል።

መቀሌ የሚገኘው የቢቢሲ ትግርኛ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል ከተሞች የሚደረጉ በረራዎች መሰረዛቸውን በከተማዋ ከሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቲኬት ቢሮ ማረጋገጥ ችሏል።

በተጨማሪም መቀሌ የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ዛሬ ወደ ቢሮ እንዳይገቡ እንደተናገራቸው ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል።

የበረራዎቹን መቋረጥ በተለመከተ እስካሁን ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጠ አስተያየት የለም።

የቢቢሲ ዘጋቢ መቀለ ወደሚገኘው አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ በማቅናት እንዳጣራው በስፈራው የተለመደው የተጓዦች እንቅስቃሴ እንደሌለ እና ከአየር ማረፊያው የጥበቃ አባላት ውጪ የሌሎች እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልጿል።

ሆኖም ለነገ አረብ እና ቅዳሜ የተቆረጡ ትኬቶች የተባለ ነገር የለን፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates