አሜሪካ
በላይ ምንነቱ ያልታወቀ ፈሳሽ የረጨው ግለሰብ በጥቃት ወንጀል ተከሰሰ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/05/2018፡- የሚኒሶታ ግዛት የኮንግረስ ተወካይ በሆነችው የኤልሃን ኦማር ላይ ምንነቱ ያልታወቀ ፈሳሽ በመርጨት ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአካባቢው የፖሊስ ኃላፊዎች አስታወቁ።
ግለሰቡ ድርጊቱን የፈጸመው ኤልሃን በከተማ አዳራሽ ውስጥ ንግግር እያደረገች ባለበት ሰዓት ነው።
ግለሰቡ በድንገት ተነስቶ በመርፌ ስሪንጅ የያዘውን ፈሳሽ ረጭቶባታል።
ስፍራው ላይ የነበረው የቢቢሲ ዘጋቢ፤ ፈሳሹ የሚሰነፍጥ ሽታ ያለው ኬሚካል መሰል ነገር እንደሆነ ገልጿል።
ፖሊስ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው አንቶኒ ጄምስ ካዝሚርቻክ የተባለው ይህ ግለሰብ 55 ዓመቱ ነው።
ግለሰቡ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውሎ ስፍራው ላይ የፎረንሲክ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
በሦስተኛ ደረጃ የጥቃት ወንጀል መከሰሱንም ፖሊስ ይፋ አድርጓል።



