አሜሪካ
ኤርትራን ጨምሮ አሜሪካ የጣለችው የጉዞ ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/04/2018፡- አሜሪካ ወደ አርባ የሚጠጉ የአፍሪካ አገራትን ጨምሮ በሌሎችም ላይ ያሳለፈችው ሙሉ የቪዛ እና የጉዞ ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
የአሜሪካ መንግሥት ከወራት በፊት ኤርትራን እና ሶማሊያን ጨምሮ በበርካታ አገራት ዜጎች ላይ የጉዞ ዕገዳ የጣለው በአገራቱ ውስጥ ባለ ደካማ የዜጎች ምዝገባ እና መረጃ አያያዝ እንዲሁም በርካቶች አሜሪካ ከሄዱ በኋላ ለረጅም ጊዜ በመቆየት እና እዚያው በመቅረታች ነው።
ይህ እርምጃ የአሜሪካንን ደኅንነት ለመጠበቅ መሆኑን የገለጸው ዋይት ሐውስ ከ54ቱ የአፍሪካ አገራት ወደ 40 የሚጠጉት ላይ እገዳ ተጥሏል።
የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ይህ በመላው ዓለም በሚገኙ አገራት ላይ የተጣለው የቪዛ እና የጉዞ ዕገዳ አገራቱ አሳማኝ መሻሻል እስኪያሳዩ ድረስ በሥራ ላይ ይቆያል።
አንዳንድ የአፍሪካ አገራት የአሜሪካ ውሳኔን በመቃወም ወደ አገራቸው በሚመጡ የአሜሪካ ዜጎች ላይ ተመሳሳይ ዕገዳን መጣላቸውን አሳውቀዋል።
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የሆኑት ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ አሜሪካዊያን ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የጉዞ ዕገዳ በመጣል የአፀፋ ምላሽ ሰጥተዋል።



