አሜሪካ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ በሱዳን ጦርነትን ለማስቆም አዲስ ጥረት እያደረገች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/03/2018፡- ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ረቡዕ ዕለት እንዳሉት አሜሪካ በሱዳን ግጭትን ለማስቆም አዲስ ጥረት እንደምትጀምር ተናግረዋል፡፡

ማክሰኞ ዕለት በዋይት ሀውስ ከሳውዲው አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን ተገናኝቶ የተወያዩት ትራምፕ ሳልማን ባደረጉላቸው ግፊት ይህን ውሳኔ ለመወሰን እብ,ንደተገፋፉ ጠቁማል፡፡

“ግርማዊነታቸው ከሱዳን ጋር የተያያዘ በጣም ኃይለኛ ነገር እንዳደርግ ይፈልጋሉ። በዚህ ውስጥ ለመሳተፍ በዕቅዴ ውስጥ አልነበረም” በማለት ትራምፕ በኬኔዲ ማዕከል በተካሄደው የአሜሪካ-ሳውዲ የኢንቨስትመንት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ተናግረዋል።

በአሜሪካ የሚመራ የኳድ አገራት ቡድን በህዳር መጀመሪያ ወር ላይ የሱዳን ፈጣን ድጋ ሰጪ የተስማማበትን የተኩስ አቁም ስምምነት ያቀረቡ ሲሆኑ ሆኖም በሱዳን መንግስት በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይተዋል፡፡

ትራምፕ ረቡዕ ዕለት በሰጡት መግለጫ አስተዳደራቸው፣ ምናልባትም ፕሬዝዳንቱ በግላቸው፣ ግጭቱን ለማስቆም አዲስ ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

“አስቀያሚ እና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር መስሎኝ ነበር። ግን ይህ ለእርስዎ እና በክፍሉ ውስጥ ላሉ ብዙ ጓደኞችዎ፣ ሱዳን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነች ተረድቻለሁ፤ እናም በሱዳን መስራት እንጀምራለን” ሲሉ ትራምፕ ቃል ገብተዋል።

የሳውዲ አረቢያ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ወደ ዋሽንግተን ከማቅናታቸው በፊት የሱዳንን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በሚቻልባቸው መንገዶች ከሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የስልክ ወይይት መድረጋቸው የዲፕሎማሲያዊ ምንጭ አረጋግጠዋል።

ውይይቱ ግጭቱን እና የሰብአዊ ቀውሱን ለማስቆም በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን አል-ቡርሃን የሳውዲ አረቢያውን ልዑል ተነሳሽነት ያለምንም ማቅማማት መቀበላቸውና አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ምንጮቹ ለሱዳን ትሪቡን ተናግሯል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates