የአሜሪካ መንግስት እኩለ ሌሊት ላይ በከፊል እንደተዘጋ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/01/2018፡- የአሜሪካ ኮንግረስ እና ዋይት ሃውስ የፌደራል በጀትን ለማራዘም በሚያስችል ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸው፣ የአሜሪካ መንግስት እኩለ ሌሊት ላይ በከፊል መዘጋቱ ታውቋል።
ሪፐብሊካን ፓርቲ በሁለቱም የኮንግረስ ምክር ቤቶች አብላጫ ድምጽ ቢኖረውም፣ በሴኔት ውስጥ ህግ ለማሳለፍ ከሚያስፈልገው 60 ድምጽ የተወሰነውን ከዴሞክራቶች ማግኘት ስላልቻለ ሁለቱም ፓርቲዎች ያቀረቧቸው ረቂቆች ውድቅ ሆነዋል።
ይህ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን በ2018 ተከስቶ ከነበረውና ለ34 ቀናት ከዘለቀው ረጅሙ የመንግስት መዘጋት በኋላ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
ልዩነቱ የተፈጠረው በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ለወራት ከዘለቀ የፖለቲካ ፍትጊያ በኋላ መሆኑም ተገልጿል።
የዴሞክራቶች የጤና መድህን ሽፋንን የሚያራዝሙ ድንጋጌዎች እንዲካተቱ ይፈልጋሉ። በተለይ በዚህ ዓመት መጨረሻ ጊዜው የሚያልቀውንና የዜጎችን ወርሃዊ ክፍያ ከፍ የሚያደርገውን “ኦባማ ኬር” የተሰኘውን የጤና መድህን ድጎማ ማስቀጠል ዋነኛ ጥያቄያቸው እንደሆነ ተገሎጿል።
ሪፐብሊካኖች ደግሞ መንግስትን እስከ ህዳር 21 ድረስ ክፍት የሚያደርግ “ንጹህ” ምንም አይነት ተጨማሪ ፖሊሲ ያልተካተተበት የበጀት ማራዘሚያ አቅርበው ስለ ፖሊሲ ጉዳዮች የሚደራደሩት በመደበኛው የበጀት ሂደት ውስጥ ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
የመንግስት መዘጋት ወደ 750,000 የሚጠጉ ሰራተኞች በየቀኑ ከስራ ገበታቸው እንዲወጡ እንደሚያስገድድ ታውቋልደ