ቻይና 26 ወታደራዊ አውሮፕላኖች እና 7 የጦር መርከቦችን በመጠቀም ታይዋንን መክበብዋ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/07/2018፡- የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው እሁድ ቀን በደሴቱ አቅራቢያ የቻይና የጦር አውሮፕላኖች በብዛት ከፍ ብለው ሲበሩ ታይተዋል።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት የበረራ ቁጥር እጅግ እንደቀነሰ ከታየ በኋላ ይህ በረራ በተከታታይ መደረጉ ስጋት እንዲፈጠር ሆነዋል።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው እሁድ ቀን በታይዋን ዙሪያ 26 የቻይና የጦር አውሮፕላኖች ተገኝተዋል፤ ከእነዚህ 16ቱ ወደ ሰሜን፣ መካከለኛ እና ደቡብ-ምዕራብ ያሉ የአየር መከላከያ መለያ ክልሎች ገብተዋል ብለዋል።
እንዲሁም 7 የባህር ኃይል መርከቦች በደሴቱ ዙሪያ ታይተዋል ብሏል፡፡
በዚህም ቻይና በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ቀውስ ተጠቅማ ታይዋንን ልትወር ትችላለች የሚል ስጋት ተፈጥረዋል፡፡
አሜሪካ በኢራን ጦርነት በተጠመደችበት ወቅት ቻይና አድፍጣ በታይዋን ወረራ ልትፈፅም ትችላለች የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደግሞ ቻይና በኢራን የተዘጋውን የሆርሙዝ ሰርጥ በማስከፈት ካላገዘች ወደ ቤጂንግ ሊደርጉት የነበሩት ጉዞ ሊዘገይ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፤
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንቋጨዋለን ብሎ ከእስራኤል በመሆን የጀመሩት የኢራን ጦርነት አሁን ሀገራት ድጋፍ እንድያደርጉ እየተማፀኑ ነው፡፡
በዚህም ቻይናን እና ጃፓንን ጥሪ ያደረጉ ሲሆኑ ጃፓን ጥያቄውን ውድቅ አድርጋለች፡፡



