ማህበራዊ

በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የ65 ሰዎች ህይወት ማለፉን ከ60 በላይ የተገመቱት ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/07/2018፡- ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ፣ ቦንኬ፣ ካምባ ዙሪያ እና ምዕራብ አባያ ወረዳዎች በሚገኙ 6 የተለያዩ ቀበሌዎች የተከሰቱ የመሬት መንሸራተት፣ ናዳ እና የጎርፍ አደጋዎችን ተከትሎ የደረሱ ጉዳቶችን እየተከታተለ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ኮሚሽኑ መግለጫው ይፋ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች አስከሬናቸው መገኘቱ የተረጋገጠውን ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ የገቡበት ባለመታወቁ በአደጋው ሕይወታቸው ማለፉ ይገመታል ብሏል።

በመሬት መንሸራተቱ ምክንያት 3ሺህ 461 ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እንደተጋለጡ አሳውቋል።

አደጋው በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት፣ ሙሉ በሙሉ የወደሙ መኖሪያ ቤቶች እና ማሳዎችን ጨምሮ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢሰመኮ ማረጋገጡን አስታውቋል።

ኢሰመኮ የመዋቾች ቁጥር 65 መሆኑን ሲያመለክት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ በስፍራው ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ መግለጫ ያወጣው ምክር ቤቱ ደግሞ 70 እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አደሃኖም ወደ ስፍራው መድኃኒት መላካቸው አስታውቀዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ በተመሳሳይ በርካታ ዜጎች ህይወታቸውን ማጣቸው ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates