በሱዳን በአንድ ሳምንት ውስጥ በድሮን ጥቃት ከ200 በላይ ሲቪሎች መገደላቸውን የተመድ ሪፖርት አመለከተ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/07/2018፡- የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኃላፊ ቮልከር ተርክ ሐሙስ ዕለት ባስተላለፉት መልእክት እ.አ.አ ከመጋቢት 4 ጀምሮ በሱዳን ከ200 በላይ ሲቪሎች በድሮን ጥቃት መገደላቸው ገልፀዋል፡፡
በሱዳን ግጭት ውስጥ ሁለቱም ወገኖች በተራቀቀ የድሮን ጦርነት ላይ ጥገኛ ሆነዋል ያለው የአልጄዚራ ዘገባ ይህም ከተባበሩት መንግስታት ተደጋጋሚ ውግዘት ቢያስከትልም የቆመ ነገር አይደለም ብለዋል፡፡
“በሱዳን ግጭት ውስጥ በርካታ ማሳሰቢያዎች፣ ማስጠንቀቂያዎች እና አቤቱታዎች ቢኖሩም፣ ሕዝብ በበዛትባቸው አካባቢዎች ሰፊ ተጽዕኖ ያላቸውን ፈንጂ መሳሪያዎችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ድሮኖችን መጠቀማቸውን በጣም ያሳዝናል” ሲሉ ተርክ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
«እነዚህን የጦር መሳሪያዎች አጠቃቀም በተመለከተ ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግን ሙሉ በሙሉ እንዲያከብሩ ጥሪዬን እቀጥላለሁ፣ በተለይም በሲቪሎች፣ በሲቪል ዕቃዎች እና በመሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የተከለከለ መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ” ሲሉ ረደምጠዋል፡፡
ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ በሱዳን የጦር ኃይሎች (SAF) እና በፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) መካከል የተፈጠረው ግጭት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንደተገደሉ እና 11 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችም ከቤታቸው እንደተፈናቀሉ መረጃዎች ያሳያሉ።
ተርክ እንዳሉት በምዕራብ ኮርዶፋን ቢያንስ 152 ሲቪሎች በፈጣን ድጋፍ ሓይሎች የድሮን ጥቃቶች መገደላቸውን ተዘግቧል፤ ከእነዚህም ውስጥ መጋቢት 4 ቀን በሙግላድ ከተማ ገበያና ሆስፒታል በደረሰባቸው ጥቃት ቢያንስ 50 ሲቪሎች መገደላቸውን ተናግረዋል።
መጋቢት 7 ቀን በRSF ቁጥጥር ስር ባለው አቡ ዛባድ እና ዋድ ባንዳ በሁለት የተለያዩ ገበያዎች ላይ በተፈፀሙ ጥቃቶች ቢያንስ 40 ሲቪሎች መሞታቸውን ተርክ ተናግረዋል።
መጋቢት 10 ቀን በአል-ሱነት በሱዳን ሰራዊት ድሮን ሲቪሎችን የጫነ የጭነት መኪና ቢያንስ 50 ሲቪሎችን መግደሉን ተዘግቧል።
“በሱዳን ውስጥ ትርጉም የለሽ ግጭት ከተጀመረ ሶስት ሙሉ ዓመታት ሊሞላው ነው፣ ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እና የኑሮ መተዳደሪያ ውድመት አስከትሏል” ብለዋል።



