“የነዳጅ እና የጋዝ ሀብታቸውን በእሳት እንዲጋይ እናደርጋለን ” ሲሉ የኢራን ባለልስጣናት ዛቱ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/07/2018፡- ኢራን በኢነርጂ መሠረተ ልማቶቿ ላይ ጥቃት የሚሰነዘር ከሆነ መላው የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና የነዳጅ እና የጋዝ ሀብት ” በእሳት እንዲጋይ ” እንደምታደርግ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጠች።
የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ይህ የቴህራን ዛቻ የመጣው ” እስራኤል በኢራን የነዳጅ ማጣሪያዎች እና የጋዝ ተቋማት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እያቀደች ነው ” የሚሉ መረጃዎች በስፋት መውጣታቸውን ተከትሎ ነው።
የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት በሰጡት ቃል ፥ የሀገሪቱ የኢነርጂ ዘርፍ ጥቃት የሚደርስበት ከሆነ ምላሹ በኢራን ብቻ እንደማይወሰንና በቀጠናው ያሉ የሌሎች ሀገራት የነዳጅ እና የጋዝ መሰረተ ልማቶችም ኢላማ እንደሚሆኑ ገልጸዋል። ”
ይህ የኢራን ዛቻ ቀድሞውንም ከፍተኛ የሆነ የዋጋ መናር እየታየበት ያለውን የዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ይበልጥ ስጋት ላይ የጣለ ሆኗል።
በሌላ በኩል ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መናሩ አሜሪካን አትራፊ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገልጸዋል። ትራምፕ ፥ አሜሪካ በዓለም ላይ ትልቋ የነዳጅ አምራች መሆኗን አመልክተው ” የዋጋው መጨምር ብዙ ገንዘብ ለሀገሬ ያስገኛል ” ብለዋል።
” ነገር ግን እንደ ፕሬዝዳንትነቴ ለእኔ በጣም ወሳኙ ነገር ክፉዋ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት በማድረግ መካከለኛው ምሥራቅን ብሎም ዓለምን እንዳታወድም ማድረግ ነው። በፍጹም ያ እንዲፈጠር አልፈቅድም ” ሲሉ ገልጸዋል።



