ኤስያ

የህንዱ ኢንዲጎ አውሮፕላን በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሲደርስ በድንገት አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ኒው ዴልሂ መመለሱ ታውቀዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/07/2018፡-  ከዴልሂ ወደ #ማንቸስተር ከተማ በመብረር ላይ የነበረው የኢንዲጎ አየር መንገድ አውሮፕላን በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሲደርስ በድንገት አቅጣጫውን በመቀየር ወደ ኋላ መመለሱ ተዘግበዋል።

በረራው አቅጣጫውን የቀየረበት ምክንያት እስካሁን በግልጽ ባይታወቅም በዛሬ ዕለተ ሰኞ ከኒው ዴልሂው ኢንዲራ ጋንዲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመነሳት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ማንቸስተር የታቀደ ጉዞ በማድረግ ላይ እንደነበር ታውቀዋል።

የበረራ መከታተያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ አውሮፕላኑ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ከተቃረበ በኋላ ድንገተኛ መመለስ (U-turn) አድርጓል ተብለዋል።

እስካሁን ድረስ ስለ አውሮፕላኑ ቴክኒካዊ ብልሽትም ሆነ ስለ ኦፕሬሽን ችግር የተሰጠ ፍንጭ የሌለ ሲሆን፣ ከአየር መንገዱም የተሰጠ ይፋዊ ማብራሪያም የለም።

በበረራው ላይ የነበሩ ተጓዦች ስለደረሰ አፋጣኝ አደጋ የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረ የተገለጸ ሲሆን፣ አውሮፕላኑ ወደ ሕንድ የአየር ክልል ከተመለሰ በኋላ ጉዞውን በሰላም ቀጥሏል።

አውሮፕላኑ በምስራቅ አፍሪካ የአየር ክልል ለመጓዝ የተገደደው በመካከለኛ ምስራቅ በተከሰተው ቀውስ ተከትሎ የአየር ክልሎች በመዘጋታቸው ምክንያተ ነው፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates