የአፍሪካ ህብረት የባህረ ሰላጤው ጥቃቶች ዓለም አቀፍ የኃይል እና የአፍሪካ ኢኮኖሚዎችን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ አስጠነቀቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/07/2018፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር እየደረገ ባለው ጦርነት ወቅት በባህረ ሰላጤው መሠረተ ልማት ላይ የሚሰነዘሩት ጥቃቶች የነዳጅ ዋጋን እያስጨመሩ እና የአፍሪካ የንግድ መስመሮችን እና የአየር መንገዶችን እያስተጓጎሉ መሆናቸውን አስጠንቅቋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ወሳኝ በሆኑ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየተባባሱ መምጣታቸውን የገለፀ ሲሆን፣ ክስተቶቹ ዓለም አቀፍ የኃይል ደህንነትን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ እና የአፍሪካ ኢኮኖሚዎችን እየነኩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ባለፈው ሳምንት በባህረ ሰላጤው ውስጥ ያለው ሁኔታ እየተባባሰ መጥቷል ያለው ኮሚሽኑ፣ ይህም ወደ ሰፊ የቀጠና ግጭት እየተስፋፋ መሆኑን አስጠንቀቅዋል።
በበቀል እርምጃው ኢራን በበርካታ የባህረ ሰላጤ ሀገራት የአሜሪካን ወታደራዊ ማዕከላት እና ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን ኢላማ እያደረገች መሆኑዋና ጥቃቶቹ ውጥረቱን ከፍ አድርገው ለዓለም ኢኮኖሚ ወሳኝ የሆኑ የኃይል አቅርቦቶች እና የንግድ መስመሮች መረጋጋት ስጋትን አስነስተዋል ብለዋል።
የህብረቱ ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ሰኞ ዕለት ባወጡት መግለጫ፣ በቀጠናው በንግድ እና በትራንስፖርት ላይ እየጨመረ የመጣውን አደጋ አጉልተው ገልጸው፣ በባህረ ሰላጤው ውስጥ የሚፈጠሩ መስተጓጎሎች በመላው አፍሪካ እየተስተዋሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና ወሳኝ የአቅርቦት ሰንሰለቶች መቆራረጥ ከአፍሪካ ኤክስፖርት እስከ ቀጠናዊ የአየር ጉዞ ድረስ ያሉ ዘርፎችን የሚነኩ ዘደገኛ መዘዞች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
“በባህረ ሰላጤው ክልል ውስጥ ያለው መረጋጋት ለአለም አቀፍ የኢነርጂ ደህንነት እና ለአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ልዩ ጠቀሜታ አለው፣ ይህም ለአፍሪካ ኢኮኖሚዎች ቀጥተኛ አንድምታ አለው” ሲሉ የህብረቱ ሊቀመንበር ተናግረዋል።



