መካከለኛ ምስራቅ

ኢራን ለሽምግልና ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥዋ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/07/2018፡- የኢራን መንግስት በወቅታዊው የቀጣናው ውጥረት ዙሪያ ለሚደረጉ ማንኛውም አይነት የሽምግልና ጥረቶች ጥብቅ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን ማቅረቡ ተሰማ።

የኢራን መንግስት ቃል አቀባይ ፋተሜህ ሞሃጄራኒ እንደገለጹት፤ ማንኛውም ሽምግልና ፍሬያማ ሊሆን የሚችለው አፋጣኝ የተኩስ አቁም ሲደረግ ፣ ጥቃቶች ሙሉ በሙሉ ሲቆሙ እንዲሁም ጥቃቱ ዳግመኛ እንደማይፈጸም የጽኑ ዋስትና ማረጋገጫ ሲሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል።

ኢራን ይህን አቋም የያዘችው የህዝቧን ደህንነት ለማረጋገጥ እና የቀጣናውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ እንደሆነም አልጀዚራ ዘግቧል።

በኢራን ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ተጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ኔታንያሁ ‘የኢራንን አገዛዝ እየሰባበርነው ነው’ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከኢራን ጋር ስለሚያካሂዱት ጦርነት በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የቴህራንን አገዛዝ “እየሰባበርነው ነው” ብለዋል።

ዋና ዓላማችን የኢራንን ሕዝብ ከአገዛዙ [እስላማዊ አብዮት] ማላቀቅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ “የመጨረሻው ውሳኔ ግን የእነርሱ ነው” ብለዋል።

“ምንም ጥርጥር የለውም እስካሁን በተወሰደው እርምጃ ሰባብረናቸዋል፤ አሁንም እርምጃችንን እንደቀጠለ ነው” በማለት በይፋዊ የኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

ፕዝዳንት ትራምፕ ሰኞ ዕለት ከበርካታ የመገናኛ ብዙኃን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉ ሲሆን በተጨማሪም በሪፐብሊካን ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡ በእነዚህ ወቅቶች ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር እያካሄደች ስላለችው ጦርነት በርካታ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

“ጦርነቱ በጣም እየተጠናቀቀ ይመስለኛል፤ እንደዚያ ማለት ይቻላል” ያሉ ሲሆን አክለውም “አሜሪካ ከተያዘለት ጊዜ በጣም ቀድማለች” ብለዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates