መካከለኛ ምስራቅ

እስራኤል ጦር በኢራን ላይ የሚያካሂደው “ዘመቻ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ መሸጋገሩን” ገለጸ፡፡

ኢትዮ ሚኒተር፡ 27/04/2018፡- የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፤ በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ወደ “ቀጣዩ ምዕራፍ እየተሸጋገረ” መሆኑን እና የቴህራን “አገዛዝን እና ወታደራዊ አቅምን ከዚህም የበለጠ የመበታተን” እርምጃውን እንደሚገፋበት ገለጸ።

አሜሪካ እና እስራኤል በሚፈጽሙት ጥቃት ኢራንን “በስትራቴጂካዊ መንገድ እየነጠሉ” መሆኑን የተናገሩት የእስራኤል ጦር ዋና አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ኢያል ዛሚር፤ “ከዚህ ቀደም ባይታየ ደረጃ” እያዳከሟት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

እስራኤልባለፉት ስድስት ቀናት “ያለ ማቋረጥ” ኢራን ላይ ጥቃት ስትፈጸም መቆየቷን አንስተው፤ “ዘመቻው ባቀድነው ፍጥነት እየሄደ ነው” ብለዋል።

ዋና አዛዡ ባወጡት መግለጫ “የአየር የበላይነትን ያረጋገጥንበትን እና የባለስቲክ ሚሳዔል መሠረታቸውን ያዳከምንበትን ድንገተኛ የጥቃት ምዕራፍ ካጠናቀቅን በኋላ፤ አሁን ወደ ቀጣዩ የዘመቻ ምዕራፍ እየተሸጋገርን ነው” ሲሉ ዕቅዳቸውን አስታውቀዋል።

“በዚህ ምዕራፍ የኢራንን አገዛዝ እና ወታደራዊ አቅሙን የበለጠ እንበታትናለን። አሁን ይፋ የማላደርጋቸው ተጨማሪ ድንገተኛ እርምጃዎች ወደፊት እንወስዳለን” ሲሉም ጽፈዋል።

ወታደራዊ አዛዡ የሊባኖስንም ጉዳይ ባነሱበት በዚህ መግለጫ፤ ሄዝቦላህ ጦርነቱን መቀላቀሉ “ስትራቴጂካዊ ስህተት” እንደሆነ ገልጸዋል።

እስራኤል በጦርነት “ግንባርም ሆነ ሊባኖስ ውስጥ በጥልቅ በመግባት በኃይል እያጠቃች” መሆኑን ተናግረዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates