የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ቀውስ ከ100 በላይ በረራዎች መሰረዙ ታወቀ፡፡
ኢትዮ ሚኒተር፡ 27/04/2018፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ እና በእስራኤል በኢራን ላይ እየተካሄደ ባለው የቦምብ ድብደባ እንዲሁም ኢራን በምትሰጠው የአጸፋ ምላሽ ምክንያት፣ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና የባህረ ሰላጤው ሀገራት በቀን እስከ 15 የሚደርሱ በረራዎችን እየሰረዘ መሆኑን አስታወቀ።
በዚህም የጸጥታ መደፍረስ ሳቢያ አየር መንገዱ በሳምንት ውስጥ ከ100 በላይ በረራዎችን ለማቋረጥ ተገዷል።
የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ተቋሙ በቀጠናው ወደሚገኙ አስር መዳረሻዎች የሚያደርገውን በረራ ሙሉ በሙሉ ሰርዟል።
ከተሰረዙት መዳረሻዎች መካከል እንደ ዱባይ እና ቴል አቪቭ ያሉት በቀን እስከ ሦስት ጊዜ በረራ ይደረግባቸው የነበሩ ሲሆን፣ እንደ ኦማን ወዳሉ መዳረሻዎች ደግሞ በቀን ቢያንስ ሁለት በረራዎች ይካሄዱ ነበር።
ከመንገደኞች በረራ በተጨማሪ የጭነት (ካርጎ) በረራዎችም መቋረጣቸውን ኃላፊው አብራርተዋል። አቶ ለማ እንዳሉት፣ በሳምንት ውስጥ የተሰረዙት የመንገደኞች እና የጭነት በረራዎች ጠቅላላ ቁጥር ከ160 በላይ ደርሷል።
አየር መንገዱ ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት ወደነዚህ ቀጠናዎች በሳምንት ከ40 ሺህ እስከ 50 ሺህ የሚደርሱ መንገደኞችን ያመላልስ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ በዚህ ያልታሰበ ቀውስ ምክንያት ተቋሙ በሳምንት እስከ 137 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ከፍተኛ ገቢ እያጣ መሆኑን ገምቷል።
አየር መንገዱ ይህንን ወቅታዊ የጦርነት ክስተት ተከትሎ የተለያዩ ማስተካከያዎችን እያደረገ ይገኛል።
ከመካከለኛው ምስራቅ መስመር የሚደርስበትን የገቢ ኪሳራ ለመቀነስ በማሰብ፣ ወደነዚህ መዳረሻዎች ይበሩ የነበሩ አውሮፕላኖችን ከግጭት ቀጣናው ርቀው ወደሚገኙ ሌሎች አማራጭ መስመሮች በጊዜያዊነት አዛውሯል።
አ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።



