መካከለኛ ምስራቅ

”እስራኤል በአንድ ሚሳኤል ትጠፋለች” – አዲስ መልክ የያዘውን የኢራን እስራኤል ጦርነት

የኢትዮ ሞኒተር ትንታኔ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/06/2018፡- አዲስ መልክ የያዘውን የኢራን እስራኤል ጦርነት

አሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት ኢራን ላይ የከፈቱት ጥቃት አሁን አሳሳቢ ደረጃ ደርሰዋል፡፡

ዛሬ አራተኛ ቀኑን የያዘው ጦርነቱ የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻማኒን ጨምሮ ከ48 በላይ የኢራን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪዎች ቢቀጥፍም፣ ከአራት በላይ የአሜሪካ ወታደሮች ቢያጠፋም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ አገራት ዜጎች ህይወት ቢበላም እስካሁን እልባት አላገኘም፡፡

ይልቅኑም አድማሱ አስፍቶ 14 አገራትን አዳርሰዋል፡፡ ኢራን የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮች ያሉባቸውና ኤሜሪካን ይደግፋሉ ያለቻቸው ሀገራትን መደብደብዋ ቀጥላለች፡፡

እስራኤል እና አሜሪካ ደግሞ በኢራን ኒዩውክሌር ጣቢያዎችና ባህር ሐይል ላይ እንዲሁም ኢራን በሚደግፈው ሄዝቦላህ ላይ ተከታታይ ጥቃቶች እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ሄዝቦላህ በበኩሉ ሦስት የእስራኤል ወታደራዊ ቦታዎችን ማጥቃቱን ገልፀዋል፡፡

በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ እስራኤል በበርካታ የሊባኖስ ከተሞች እና አካባቢዎች ላይ ለምትፈጽመው ጥቃት እና ወረራ “ምላሽ ሰጥቻለሁ” ብሏል።

በጎላን ተራሮች የሚገኘውን ናፋህ የጦር ሰፈር፣ ሜሮን እና ራማት ዴቪድ የአየር ኃይል የጦር ቦታዎችን በሚሳኤል እና በድሮን ማጥቃቱን ሄዝቦላህ ገልጿል።

እስራኤል በሚሳኤል ከምትፈጽመው ጥቃት በተጨማሪ ወደ ሊባኖስ እግረኛ ጦሯን በማስገባት “ተጨማሪ ቁልፍ አካባቢዎችን” እንደምትይዝ አስታውቃለች፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦሩ ወደ ሊባኖስ ገብቶ “ተጨማሪ ቁልፍ አካበቢዎችን” እንዲቆጣጠር ማዘዛቸውን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ገልፀዋል።

የእስራኤል እግረኛ ጦር ወደ ሊባኖስ እንዲገባ የታዘዘው በእስራኤል ድንበር አካባቢ የሚገኙ ማኅበረሰቦች ላይ የሚተኮሰውን ሮኬት ለመከላከል በሚል ነው።

የእስራኤል ጦር በሊባኖስ በሚገኙ የሔዝቦላህ ዒላማዎች ላይ የሚወስደውን የኃይል እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

እስራኤል በቴህራን እና በቤሩት በሚገኙ “የወታደራዊ ኢላማዎች” ላይም አዲስ እና መጠነ ሰፊ የአየር ድብደባ መፈጸሟን አስታውቃለች።

በሌላ በኩል በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ በሁለት የኢራን ድሮኖች መመታቱን የሳዑዲ መከላከያ ሚኒስቴር ያረጋገጠ ሲሆን፤ በጥቃቱም “ውስን” የሆነ የቃጠሎ አደጋ ደርሷል።

እንዲሁም በባህሬን በሚገኘው የአሜሪካ አየር ኃይል ጣቢያ ውስጥ የሚገኝ የአዛዥ እና የሠራተኞች ሕንፃ መውደሙን ተዘግበዋል።

 

የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት በሳዑዲ ዓረቢያ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ከኢራን በተፈፀመ ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል፡፡

ቫንቶር ያወጣቸው የሳተላይት ምስሎች በምሥራቅ ራስታኑራ ከተማ በሚገኘው የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከላዊ አካባቢ በሚገኙ የማቀዝቀዣ ማማዎች ዙሪያ የእሳት እና የቃጠሎ ምልክቶች ታይተዋል።

ቦታው የተለያዩ የማከማቻ ክፍሎችን ከጣቢያው ማዕከላዊ ምሰሶ ጋር የሚያገናኙ ተከታታይ ቱቦዎች ያሉት ሲሆን፣ እነዚህም በተለምዶ አራት ታንከሮችን በአንድ ጊዜ መሙላት የሚችሉ ናቸው።

ማጣሪያው በቀን 550,000 በርሜል ነዳጅ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን በጥቃቱ ምክንያት የነዳጅ ማጣሪያው ለጊዜው ተዘግተዋል።

እንዲሁም ኢራን በአሜሪካው የጀት ተሸካሚ ግዙፉ የአብርሃም ሊንኮን መርከብ በአራት ሚሳኤሎች ጥቃት መፈጸምዋ አስታውቃለች፡፡

ሌላው ትልቁ ዓለምን ያስደነገጠው የኢራን ውሳኔ፤ የዓለሙ ጠባብ የነዳጅ መተላለፊያ የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ መዝጋትዋ ነው፡፡

ይህ ከ20 በመቶ ወይም አንድ አምስተኛ የዓለም ነዳጅ የሚተላለፍበት ጠባብ መስመር ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ አውሮፓና አፍሪካ የሚገባውን ነዳጅ ይተላለፍበታል፡፡

የኢራን ባለሥልጣናት ለዓለም የኃይል አቅርቦት ወሳኝ በሆነው በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ መዘጋቱንና በመስመሩ በሚያልፉ መርከቦች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መዘጋጀታቸው ዝተዋል።

በዚህ መስመር ለማለፍ በሚሞክር ማንኛውም መርከብ ላይ ‹‹እሳት እንለኩሳለን›› ሲሉ አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

የሆርሙዝ ሰርጥ መዝጋት የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲንር ያደርገዋል።

በዚህም ዛሬ ቀን ላይ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ሰርጥ በሆንዱራስ ሰንደቅ ዓላማ ስትጓዝ የነበረች ” አቴ ኖቫ ” የተባለች የነዳጅ ጫኝ መርከብ በ2 ድሮን መትቶ እንድትነድ ማድረጉን ገልጿል።

እስካሁን 5 መርከቦች በኢራን እንደተመቱ የተገለፀ ሲሆን 150 ደግሞ ወደኃላ እንዲመለሱ መገደዳቸው ታውቀዋል፡፡

የኢራን እስላማዊ አብዮት ዘብ ዋና አዛዥ አማካሪ የሆኑት ኢብራሂም ጃባሪ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው መርከቦች “ወደ ቀጠናው መምጣት የለባቸውም። ከባድ የሆነ ምላሽ ከእኛ ይጠብቃቸዋል” ሲሉ ዝተዋል።

ጃባሪ አሜሪካ “የቀጠናውን የነዳጅ ዘይት ተጠምተዋል” ያሉ ሲሆን ኢራን “በቀጠናው የሚገኙ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧዎችን ታጠቃለች፤ ከቀጠናው ነዳጅ እንዲላክ አትፈቅድም” ብለዋል።

የመን የሚገኘው የሁቲ ዓማፂ ቡድን ድግሞ የቀይ ባህር ባብ ኤል ማንዴብ መስመር ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀምረዋል፡፡ ይህ መስመር ቀይ ባሀርን ከኤደን ባህረ ሰላጤ የሚያገናኝ ወሳኝ የንግድ መተላለፊያ መስመር መሆኑ ይታወቃል፡፡

 

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ደናልድ ታረምፕ በቀናት አጠናቅቀዋለሁ ብሎ በኦፕሬሽንስ ስም የገቡበት የኢራን ጥቃት አሁን በአጭሩ የሚቋጭ አይመስልም፡፡

ትራምፕ ጦርነቱ ከአራት እስከ አምስት ሳምንታት ሊፈጅ እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቅዳሜውን ጥቃት “የመጨረሻው ዕድል” ሲሉ መግለጻቸዉን በመጥቀስ፤ ከባዱ የአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት ‹‹ገና ወደፊት ይመጣል›› ሲሉ ዝተዋል።

ለረጅም ጊዜ ሊያዋጋት የሚችል ወታደራዊ አቀም እንዳላት ትራምፕ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ እንዳጋሩት ከሆነ አገራቸው “የተራዘመ ጦርነት” ማድረግ የሚያስችሉ የ”መካከለኛ እና ከፍተኛ ደረጃ” የጦር መሣሪያዎች እንዳላት በመግለጽ በእነዚህ አቅርቦቶች ብቻ መዋጋት እንችላለን ብለዋል።

“የእነዚህ የጦር መሣሪያዎች ከፍተኛ ክምችት አለን። ዩናይትድ ስቴትስ በቂ ክምችት አላት። እና ለማሸነፍ ዝግጁ ናት. . . ” ሲሉ ትራምፕ በማኅበራዊ ድረገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

ኢራንም ምን አያችሁ፤ ገና ፅዮናዊያንን የሚያጠፋ መሳሪያ እጠቀማለሁ ስትል እየዛተች ትገኛለች፡፡

የተለያዩ አገራት በዚህ እየተስፋፋ እየመጣ ያለውን ጦርነት ኢጃቸው ሊያስገቡ እንደሚችሉ ተሰግተዋል፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ኢራን ሚሳኤል ከጠየቀትን ለመስጠት ዝግጁ ነን፤ እስራኤልን በአንድ ሚሳኤል ልትጠፋ ትችላለች ብለዋል፡፡

ቻይናም ከባድ ማስጠንቀቂያ እየሰጠች ትገኛለች፡፡ ቻይና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርዋ በኩል ባወጣችው መግለጫ የኢራን ሉአላዊነት መከበር እንዳለበት በመናገር አሜሪካ የ240 ታሪክዋ ጦርነትና ጠብ ኣቻሪነት ነው ሲል ወርፈዋል፡፡

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር፤ ከሰማይ በሚዘነብ ጥቃት የመንግሥት ለውጥ እንደሚመጣ አላምንም በማለት በፓርላማ ቢናገሩም፣ የአሜሪካ ጦር በኢራን በሚገኙ የሚሳኤል ጣቢያዎች ላይ ለሚያደርገው “የመከላከያ” ጥቃት ግን የብሪታንያ የጦር ሰፈሮችን እንዲጠቀም ፈቅደዋል። ጦርነቱ ‹‹መቼ›› ወይም ‹‹እንዴት›› እንደሚጠናቀቅ መገመት ከባድ ነው ሲልም ስጋታቸው ገልፀዋል።

የዐረብ ሃገራት በበኩላቸው በተቀናጀ መንገድ ኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እያጤኑ መሆናቸው ተገልፀዋል፡፡

በኢራን ጥቃት ከፍተኛ ውድመት እያስተናገዱ የሚገኙት ሳውዲ ዓረቢያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ አሜሪካ የምትሰጠው ከለላ ለእስራኤል ያደላ መሆኑ በመጠቆም የአየር ክልላቸው እንድትከላከልላቸው ጠይቀዋል፡፡

ይህ በርካታ አገራት እያደረሰ ባለው ጥቃት ስጋት ያደረባቸው በርካታ አገሮች ዜጎቻቸው ከመካከለኛ መስራቅ እንዲዎጡ ጥሪ እያቀረቡ ትገኛሉ፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ 14 አገራት በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ አዝዘዋል።

አሜሪካውያን “ሊያጋጥሙ በሚችሉ ከባድ አደጋዎች ምክንያት” ከአስራ አራቱ አገራት “ያሉ የትራንስፖርት አመራጮችን በመጠቀም አሁኑኑ” ለቅቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።

የአሜሪካ ዜጎች በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ የታዘዙባቸው አገራት ባህሬን፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ እስራኤል፣ የፍልስጤም ግዛቶች፣ ዮርዳኖስ፣ ኩዌት፣ ሊባኖስ፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሶሪያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የመን ይገኙባቸዋል።

በኩዌት የሚገኘው ኤምባሲ ለየትኛውም የቆስንስላ ጉዳዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ማቋረጡን ማስታወቁ ይታወሳል።

 

ይህ በአመዛኙ በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ እየተደረገ ያለው ጦርነት መቋጫው የት ሊሆን እንደሚችል የብዙዎች ስጋት ሆነዋል፡፡

የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት አሜሪካ እና እስራኤል የጀመሩት ጦርነት ቀጠናው ከማውደም ያለፈ ፖለቲካዊ ፋይዳ ሊኖረው አይችልም፡፡

አሜሪካ እና እስራኤል ኢራንን ለማጥቃት የሄዱበትን መንገድ የሚተቹት ተንታኞቹ አሜሪካ እና እስራኤል ድርድር በሚል ሰበብ አዘናግቶ ጥቃት ፈፅሞባታል ይላሉ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝንት ዶናልድ ትረምፕ ባደረጉት ጥሪ መሰረት በኦማን ባለስልጣናት አደራዳሪነት በጄኔቫ ሲካሄድ የነበረው የአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ጥሩ ውጤት እያስገኘ እንደሆነ የአሜሪካ ባለስልጣናት ሳይቀሩ ሲገልፁ ነበር፡፡

የተቀሩ ስምምነት ላይ ያልተደረሰባቸው ነጥቦች ቢኖርም አብዛኞቹ ላይ ጥሩ መቀራረብ እንደነበር የገለፁት የሁለቱ አገራት ተደራዳሪዎች ሁለተኛ ዙር ለመወያየት ቀጠሮ በያዙበት ወቅት እስራኤል እና አሜሪካ በኤራን ላይ የቦምብ መአት ያዘነቡባት፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በጀመረው ጥቃት የኢራኑ የሃይማኖታዊ ስርዓቱ የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻማኒን ጨምሮ በርካታ መሪዎች ተገድለዋል፡፡

በወቅቱ መሪዎቹ ስብሰባ እንደሚያደርጉ የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲአይኤ ያውቅ እንደነበረ እና መረጃው ለእስራኤል አሳልፎ በመስጠት ጥቃቱ እንድትፈፅም እንዳደረጋት መረጃዎች አሳይተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ሞሳድን እንዲሰልይ የተቋቋመው የኢራኑ የስለያ ቡድን በሞሳድ አባል የሚራ ነበረ የሚል መረጃ መውጣቱ ጉዳዩ የአሜሪካ እና እስራኤል ሳይሆን የኢራን የውስጥ የፖለቲካ ቅሌት እንደሆነ እየተገለፀ ይገኛል፡፡

ኢራናዊያን የስርአት ለውጥ እንዲመጣ በተደጋጋሚ በአደባባይ ተቃውማቸው ሲያሰሙ ነበሩ ቢሆንም አሜሪካ እና እስራኤል በፈፁመት ጥቃት ግን ከጥቂት ተቃዋሚ ቡድኖች አብዛኞቹ ኢራናዊያን ላይ ቁጣ ፈጥረዋል፡፡

በዚህ የአሜሪካ እና እስራኤል ከሰማይ የሚዘንበው ቁምቡላ ሳይፈሩ አደባባይ በመውጣት ድምፃቸው አሰምተዋል፡፡

ውድመት ለፅዮናዊያን ማለትም እስራኤላዊያን ሲል ተቃውማቸው ከፍ አድርጎ አሰምተዋል፡፡

አሁን የአሜረካ – እስራኤል እና ኢራን ጦርነት አራተኛ ቀኑን ይዘዋል፡፡

በሁለቱም ጎራ በርካታ አገሮች ተሰባስበዋል፡፡

ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይነሳ ይሆን የብዙዎች ስጋት ነው፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates