ፖለቲካ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ተካሄደ።

ውሳኔውን እንዲቀለበስ እና የትግራይ ግዛቶች ወደ ቅድመ 2013 እንዲመለሱ ሰልፈኞቹ ጠይቋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 2-0/06/2018፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔን በመቃወም በዛሬው ዕለት በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ታውቋል፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፌደሬሽን ምክር ቤት ደርሶኛል ባለው ደብዳቤ መሠረት በአማራና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል የጥያቄ የሚነሳባቸው ስፍራዎች ከትግራይ ክልል ውጪ ሆነው በቀጥታ ለፓርላማ ምርጫ እንዲደረግባቸው መወሰኑን ይታወሳል፡፡

የሁመራ፣ የአዲረመፅ፣ የኮረም አፍላ፣ የፀለምትና የራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ ምክር ቤቱ መወሠኑን ለቦርዱ አሳውቋል።

የክልል ምክር ቤት ምርጫው በአካባቢዎቹ ላይ የተነሣው የይገባኛል ውዝግብ በሕገ-መንግሥት ውሣኔ ሲፈታ አመቺ ጊዜ ተመርጦ ወደፊት እንዲካሄድ መወሠኑንም እንዲሁ ምከር ቤቱ አሳውቋል።

ይህንን ተከትሎ የትግራይ ሊሂቃን ውሳኔውን የተቃወሙት ሲሆን የስምረት እና ወለዶ ፓርቲዎች ደግሞ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ትናንት የካቲት 19 እንዲታገድ ሆኗል። ዛሬ የካቲት 20 በበርካታ የትግራይ ከተሞች የፌደሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates