በኬኒያ ቁጣ የቀሰቀሰ የፓስፖርት ቅሌት

ኢትዮ ሞኒተር፡ 2-0/06/2018፡- የኬንያ የቀድሞ ዋና ዳኛ፡ በተመድ፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ለተጣለባቸው የመሐመድ ዳጋሎ ወንድም ፓስፖርት ሰጥቶ መገኘታቸው በአገሪቱ አነጋጋሪ ሆነ።
ተግባሩ የኬንያን ሉዓላዊነትን የሚያዋርድ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ገፅቷን የሚያበላሽ ተብሏል።
እ.ኤ.አ. የካቲት 26፣ 2026 በወጣው መግለጫ፣ የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች አዛዥ መሐመድ ሃምዳን “ሄሜቲ” ታናሽ ወንድም የሆኑቱን አልጎኒ ሃምዳን ዳጋሎ ሙሳ የኬንያ ፓስፖርት እንዳላቸው የሚገልጽ አስደንጋጭ መረጃ መውጣቱ ከፍተኛ ቁጣ ፈጥሯል።
ፓስፖርቱም በቀድሞው የኬንያ ዋና ዳኛ እና የፕሬዚዳንት እጩ ዴቪድ ኬ. ማራጋ የተሰጠ መሆኑ እየተገለፀ ነው።
አልጎኒ ሃምዳን ዳጋሎ ሙሳ” የኬንያ ፓስፖርት ቁጥር AK1586127 እንዳላቸው የሚያመለክቱ ሪፖርቶችን መውጣታቸው ተከትሎ ነው ጉዳዩ አነጋጋሪ የሆነው።
አልጎኒ በሱዳን የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ዘመቻ ውስጥ የጦር መሳሪያ ግዥ እና ሎጂስቲክስ ቁልፍ ሰው እንደሆኑ የሚገለፅ ሲሆን ይህም በኤል ፋሸር ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር ተያይዞ ማዕቀብ ተደርጎባቸዋል። እንደ መግለጫው ከሆነ፣ በዱባይ የሚገኙት ነጋዴ እና ከፍተኛ የRSF የሎጂስቲክስ ኦፊሰር የሆኑት አልጎኒ ዳጋሎ የተሰጣቸውን የኬኒያ ፓስፖርት በገለልተኛ አካል ከተረጋገጠ ፓስፖርቱን ለሰጡት ዳኛ ማራጋ ብቻ ሳይሆን ኬንያ ሊደርስ የሚችለው ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ከፍተኛ እንደሚሆን ይገመታል።



