የተለያዩ

ኢንሳ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየተፈፀመ እንደሚገኝ አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 2-0/06/2018፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ኢንሳ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም ሰባተኛውን ጠቅላላ የምርጫ ሂደትን ተገን በማድረግ፣ አጥፊዎች ስልታቸውን ይበልጥ በማወሳሰብ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየፈጸሙ እንደሚገኝ ከሚደርሱኝ መረጃዎችና የሳይበር ደህንነት ትንተናዎች ማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል።

አስተዳደሩ ባስተላለፈው አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክቱ ላይ ጥቃቱ በተለይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ተማሪዎችን፣ በርቀት ሆነዉ በዲጂታል አማራጮች የሚማሩ ግለሰቦችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን ገልጿል።
የመረጃ መንታፊዎች ከሚጠቀሙባቸዉ ዋና ዋና የጠለፋ ስልቶች መካከልም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደጋፊ በመምሰልና የፓርቲዎችን አርማ በመጠቀም “ለፓርቲያችን ድጋፍዎን እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ይግለጹ” ወይም “የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናችንን ይቀላቀሉ” የሚሉ አሳሳች መልዕክቶችን መላክ አንዱ መሆኑን ጠቁሟል።
በተጨማሪም “የምርጫ ጣቢያዎትን ለማወቅ”፣ “የዕጩዎችን ዝርዝር ለማየት” ወይም “የምርጫ ውጤቶችን በቅድሚያ ለማግኘት” የሚሉ አሳሳች ማስፈንጠሪያዎችን (Links) በመጠቀም የተጠቃሚዎችን የዋትስአፕ አካውንት በቁጥጥራቸው ስር እንደሚያውሉ አመልክቷል።
Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates