ፖለቲካ
ውሳኔው ታገደ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/06/2018፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የእግድ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ መካከል እየተካሄደ ባለው የሕግ ክርክር ላይ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በቦርዱ ውሳኔ ላይ ጊዜያዊ እግድ መጣሉ ታወቀዋል።
ፓርቲው በየካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባስገባው የቃለ መሐላ አቤቱታ የቦርዱ ውሳኔ እንዲታገድ ጠይቆ እንደነበር ታውቀዋል።
ምርጫ ቦርድ በየካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል አከራካሪ በሆኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔን ተከትሎ ፓርቲው ባስገባው አብየቱታ ክርክሩ እስኪያልቅ ድረስ ታግዶ እንዲቆይ ፍርድ ቤቱ አዟል።
ፍርድ ቤቱ አምስት የምርጫ ክልሎች: ማለትም ሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም አፍላ፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው በቀጥታ የፓርላማ ምርጫ እንዲካሄድባቸው በተላለፈውን ውሳኔ በጊዜያዊነት አግዷል።
ፍርድ ቤቱ እግዱን ያስተላለፈው ከዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ የቀረበውን የእግድ አቤቱታ ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።
ስምረት ፓርቲ አቤቱታውን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው በፕሬዝዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል ነው።



