የተለያዩ

አራት የደቡብ ሱዳን ዜጎችና ሁለት ኢትዮጵያውያን ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/06/2018፡- መነሻቸውን ደቡብ ሱዳን በማድረግ ሕገ-ወጥየጦር መሣሪያዎችን ሲያዘዋውሩ የነበሩ አራት የደቡብ ሱዳን ዜጎች እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ግብረ-አበሮቻቸው ከነኤግዚቢታቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የ ጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱዋች ጋትኮት እንደገለጹት፤ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ በኑዌር ብሔረሰብ ዞን ላሬ ወረዳ ውስጥ ነው።

በኤግዚቢትነት የተያዙት የጦር መሣሪያዎች ዝርዝር ሁለት አርፒጂ ላውንቸር የቡድን የጦር መሣሪያ፣ አንድ ብሬን የቡድን መትረየስ እና ዘጠኝ የአር.ፒ.ጂ ላውንቸር ቦምቦች (ቁንቡላ) መሆናቸው ተገልጿል።

በመሣሪያ ዝውውሩ ተጠርጥረው የተያዙት አራቱ የደቡብ ሱዳን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ሲሆኑ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ፑልኮድ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ኢትዮጵያውያን ተቀባይና ግብረ-አበሮችም አብረው በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ተብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates