የተለያዩ

በኢራን ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሳ የሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/06/2018፡- ​ዛሬ በኢራን ኢስፋሃን ግዛት አንዲት ወታደራዊ ሄሊኮፕተር በድንገት መከስከስዋ ተገለፀ።

ለልምምድ ተግባር ስታገልግል የነበረችው ሄሊኮፕተርዋ፣ በዶርቼህ ከተማ በሚገኝ የፍራፍሬና አትክልት ገበያ አቅራቢያ በሚገኝ ቅጥር ግቢ ውስጥ መውደቅዋ ተገልፀዋል።

​በደረሰው አደጋ በሄሊኮፕተሯ ውስጥ የነበሩት አብራሪና ረዳት አብራሪ ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

በተጨማሪም በገበያው አካባቢ የነበሩ ሁለት የንግድ ሰራተኞች ለህልፈት መዳረጋቸውን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች አረጋግጠዋል።

አደጋው የተከሰተው በቴክኒክ ብልሽት እንደሆነ የሚገመት ሲሆን፣ የነፍስ አድን ሰራተኞች በስፍራው ተገኝተው የተነሳውን እሳት ተቆጣጥረዋል።

ኢራን በማዕቀብ ምክንያት ለአሮጌ አውሮፕላኖቿ መለዋወጫ በማጣቷ መሰል የአየር ላይ አደጋዎች በተደጋጋሚ እያጋጠሟት እንደሚገኙ ይገለፃል።

ባለስልጣናት የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ ጀምረናል ብለዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates