ማህበራዊ

በግብፅ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ለእስርና ለከፋ ስቃይ መጋለጣቸው አንድ ሰብአዊ መበት ተሟጓች ድርጅት አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 17/06/2018፡- በግብፅ የሚገኙ ከ3,000 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች ለእስር ፣ ለጾታዊ ጥቃትና ለከፋ የማሰቃየት ድርጊት መዳረጋቸው አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ።

ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ አገሪቱን እየመሩ ያሉትና እስካሁንም ምርጫ አካሂደው የማያውቁት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዜጎቻቸውን ለላልተወሰነ ጊዜ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚዳርጉ በመሆኑ በርካታ ወጣቶች አገሪቱን ጥለው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል ነው ያለው መረጃው።

ሂዩማን ራይትስ ኮንሰርን – ኤርትራ (HRCE) የተሰኘው ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ ካለፈው ጥር ወር መጀመሪያ ጀምሮ ከ3,000 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች በግብፅ ተይዘው ታስረዋል።

ድርጅቱ የሰበሰባቸው ምስክርነቶች እና ፎቶግራፎች እንደሚያሳዩት፣ ታሳሪዎቹ “በድብደባ፣ በሙቅ ውኃ እና በኬሚካሎች በሚደርስ ቃጠሎ” እንዲሁም በጾታዊ ጥቃት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። በእስር ላይ በነበረች አንዲት እናት ላይ በደረሰ እንግልት ምክንያት ሁለት ታዳጊ ልጆች ሕይወታቸው ማለፉን ድርጅቱ ገልጿል።

በተጨማሪም አንዳንድ ስደተኞች በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ስደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) የተመዘገቡ ቢሆንም፣ ከግዳጅ ስደትና ከእስር ሊጠበቁ ሲገባ በግብፅ ባለሥልጣናት ወደ ኤርትራ ተላልፈው እየተሰጡ መሆኑ ተመልክቷል።

እንደ ድርጅቱ መረጃ፣ በኤርትራ ውስጥ ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን እና የሃይማኖት አናሳ ቡድኖችን ጨምሮ ከ10,000 በላይ የህሊና እስረኞች ይገኛሉ። ብዙዎቹ ያለምንም የፍርድ ቤት ሂደት ለዓመታት በእስር ላይ እንደሚገኙም የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት ዘገባ ያሳያል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates