አፍሪካ

ቻድ ከሱዳን ጋር የሚያወስናትን ድንበር መዝጋትዋ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 17/06/2018፡- ቻድ ከሱዳን ታጣቂዎች በተደጋጋሚ የሚደርስን ጥቃት ለመከላከል በሚል ከአገሪቱ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች።

የቻድ መንግሥት ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን ድንበር የዘጋው አል ቲና በተባለው የድንበር ከተማ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እና የሱዳን ጦር አጋር በሆኑ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ከተከፈተ በኋላ ነው።

የአገሪቱ መንግሥት ድንበሩ ለምን ያህል ጊዜ ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ አላስታወቀም።

ቻድ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ለሰብዓዊ ድጋፎች ከሚደረግ ዝውውር ውጪ ማናቸውንም የሰው እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን አግዳለች።

ቻድ በጦርነት ወደ ምትታመሰው ሱዳን የሚገባ እርዳታ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሠራተኞች ዋነኛ መተላለፊያ ብትሆንም፤ በተደጋጋሚ የጎረቤት አገር ሱዳን ግጭት ወደ ግዛቷ በመግባት የዜጎቿን ደኅንነት አደጋ ላይ ጥሏል።

የቻድ ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር የሱዳን ግጭት ወደ አገራቸው እንዳይስፋፋ ለመከላከል እና የአገሪቱን ዜጎች እና ስደተኞችን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ድንበሩ እንዲዘጋ መወሰኑን ገልጿል።

የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ቅዳሜ ዕለት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በድንበር ከተማዋ አል ታይን የሚገኝ የቻድ ጦር ካምፕ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ዘግበዋል። መንግሥት ግን በጉዳዩ ላይ ምንም ያለው ነገር የለም።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates