ዲፕሎማሲ

ሳውዲ ዓረቢያ እና ኢትዮጵያ በተለያዩ ጉዳዮች መወያታቸው ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 16/06/2018፡- ሳዑዲ_ዓረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአስመራ ጉብኝት መልስ በአዲስ_አበባ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር ተወያዩ::

የሳዑዲ ዓረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አብዱልከሪም አል ካሪጅ፣ በአስመራ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ከተወያዩ ከአንድ ሳምንት በኋላ አዲስ አበባ በመግባት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መምከራቸው ተገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ሁለቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ስላለው “ጠንካራ እና ለረጅም ጊዜ ስለቆየው የሁለትዮሽ ግንኙነት” ዙሪያ መወያየታቸውን ጠቅሶ፣ ግንኙነቱን ወደ “አዲስ የላቀ ደረጃ” ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል ብሏል።

በተጨማሪም በጋራ ፍላጎት ላይ በተመሰረቱ ቀጠናዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳብ ተለዋውጠዋል ሲል አክሏል።

የሳዑዲው ሚኒስትር በአዲስ አበባ ውይይት ያከናወኑት፣ በገልፍ አገራት እና በአፍሪካ ቀንድ አገራት መካከል እየጨመረ የመጣውን ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ባለፈው ሳምንት በአስመራ ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates