ኢኮኖሚ

ትራምፕ በዓለም አቀፍ ምርቶች ላይ የ15 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ መጣላቸው ተሰማ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 16/06/2018፡- ትራምፕ ከውጭ ወደ ሀገሪቱ በሚገቡ ማናቸውም ምርቶች ላይ የሚጣለውን የጉምሩክ ታሪፍ ወደ 15 በመቶ ከፍ ማድረጋቸውን አስታወቁ።

ይህ ውሳኔ የተሰማው የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል የታሪፍ ጭማሪን በተመለከተ ያስተላለፏቸውን ውሳኔዎች ውድቅ ካደረገ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።

ትራምፕ ቀደም ሲል የታሪፍ መጠኑ 10 በመቶ ይሆናል ብለው የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን መጠኑን ወደ 15 በመቶ አሳድገውታል። ​

ፕሬዝዳንቱ ይህንን እርምጃ የወሰዱት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መከፋታቸውን በገለጹ ማግስት ነው።

ትራምፕ የፍርድ ቤቱን ብይን “አሳፋሪ” ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ውሳኔው በሁለተኛው የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ለአስተዳደራቸው የደረሰ ትልቅ የፖለቲካ ምት መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ አዲሱ የ15 በመቶ ታሪፍም ፍርድ ቤቱ ለጣለባቸው ገደብ እንደ አጸፋዊ ምላሽ ተወስዷል። ​ ይህ አዲስ የታሪፍ ተመን ከፊታችን ማክሰኞ የካቲት 17 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንቱ ይህንን መመሪያ የኮንግረስን ፈቃድ ሳይጠይቁ ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉት ለአምስት ወራት ብቻ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ግን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱን ይሁንታ ማግኘት ይኖርባቸዋል።

​ይህ የትራምፕ ውሳኔ በዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በተለይም በአሜሪካ ገበያ ላይ የሚሸጡ የውጭ ምርቶች ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates