ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ ማቅናታቸው ተሰማ፡፡

ኢትዮ ሚኒተር፡ 11/06/2018፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ በዛሬው ዕለት ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአካባቢው በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

‘’ዛሬ በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የለማ የሙዝ እርሻ ከባቢን ጎብኝቻለሁ።‎ አርሶአደሮች በፍጹም ጽናት፣ ቅንጅት እና ትብብር አካባቢያቸውን በቀየረ ስራ በመመልከቴ ደስ ብሎኛል‘’ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የተመለከትነው የእርሻ ስራ፤ የአካባቢ መሬትን እና የውኃ ኃብትን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው ያሉት ሲሆኑ ባህላዊ የመስኖ ዘዴዎችን በመጠቀም እና በቅርብ ያለ ኃብትን በሚገባ ጥቅም ላይ በማዋል ማኅበረሰቡ ውጤታማ እና ተስፋ ሰጪ የግብርና ማዕከል መፍጠር እንደሚቻል አስረድተዋል።

በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማት የአርሶአደሮችን ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ ለማድረስ የፈጠረውን እድል መመልከት እጅግ የሚያበረታታ ነው።

ይኽ እድገት የልማት ጥረቶች ከአካባቢው ማኅበረሰብ ፍላጎት እና አቅም ጋር በቅርበት ሲናበቡ ሊገኝ የሚችለውን ውጤት በግልጽ የሚያሳይ ነው ማለታቸው የመንግስት ሚድያዎች ዘግበዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates