
ኢትዮ ሚኒተር፡ 11/06/2018፡- በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ጌልስኒክርቸን ከተማ ውስጥ ሀይ ስትሪት የተባለ ባንክ ግድግዳውን ሰርስረው በገቡ ሌቦቹ ከ3,000 በላይ ጥብቅ የንብረት ሳጥኖችን መዝብረዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ ወስድዋል ተብለዋል።
ዘረፋው አንድ ወር ቢያልፈውም ፖሊስ ግን ተጠርጣሪዎችን እስካሁን መያዝ እንዳልቻለ ተገልፀዋል፡፡
እንዴት ማንም ሰው ስርቆቱን አላስተዋለም? የባንኩ ሠራተኞች በምዝበራው እጃቸው ሊኖርበት ይችላልን? የባንኩ ግድግዳ ሲቦረቦር ማንም ሳይሰማ የቀረው እንዴት ነው?
ሌቦቹ ጥብቅ ቁሳቁስ የሚገኝባቸው ሳጥኖች የት እንዳሉ በትክክል ማወቅ የቻሉት በምን መንገድ ነው? የባንኩ የደኅንነት ጥበቃስ የተ ነበረ? የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች እስካሁን መልስ አላገኙም፡፡
መርማሪዎች እንደሚሉት፤ ሌቦቹ የባንኩን ግድግዳ ቦርቡረው የገቡት ከባንኩ አጠገብ በሚገኝ የመኪና ማቆሚያ በኩል ሊሆን ይችላል።
በተደራራቢ ሕንጻዎች ላይ ከሚገኘው የመኪና ማቆሚያ በኩል የባንኩን ግድግዳ መሰርሰር እንደቻሉ መላ ምት ያስቀመጡት መርማሪዎች፤ ሌቦቹ በመኪና ማቆሚያው በኩል የሚገኝ በርን አልፈው እንደገቡም ይገምታሉ።
ዝርፊያው የተፈጸመው በታኅሣሥ ወር አጋማሽ ላይ በሚገኙ ቀናት ውስጥ እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን ታኅሣሥ 27 የከተማዋ የእሳት አደጋ መከላከያ ተቋም እንዲሁም በግል የደኅንነት ጥበቃ የሚሰጥ ድርጅት ጥቆማ ደርሷቸዋል እንደነበረ ተረግግጠዋል።
የደረሳቸው ጥቆማ ባንኩ ውስጥ እሳት እንደተነሳ የሚጠቁም ነው። ይህም በሌቦቹ እንቅስቃሴ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መርማሪዎች ገልጸዋል።
ያም ሆነ ይህ ግን በጀርመን አገር የተፈፀመው የባንክ ዝሪፊያ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅና የተራቀቀ ተብለዋል፡፡


