ዲፕሎማሲ

የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጠይፕ ኤርዶሃን አዲስ አበባ ገቡ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/06/2018፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ወደ ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ በማለት ሞቅ ያለ አቀባበል ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ይህ ታሪካዊ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባለፈ፣ በሁለቱ ጥንታዊ ሀገራት መካከል ያለውን “ጥልቅ የአጋርነት ጥንካሬ” የሚያንጸባርቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
“ይፋዊ የስራ የጉብኝት ልውውጣችን በቱርክዬ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጥልቅ የአጋርነት ጥንካሬ የሚያንጸባርቅ ነው።
በአንካራ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክሩ እና ዘላቂ ትስስርን የሚያረጋግጡ ውጤታማ ውይይቶች እንዲኖሩን እመኛለሁ”ብለዋል።
Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates