የአየር ንብረት አካባቢ

“ምንም ዓይነት የፕላስቲክ ከረጢት ወይም ፌስታል አልተፈቀደም” ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስጠነቀቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/06/2018፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ለፕላስቲክ ከረጢት የተሰጠውን ትርጉም በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም፣ የተፈቀ የፕላስቲክ ከረጢት ዓይነት እንዳለ ተደርጎ የሚነገሩ መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን አስታውቋል።

ትላልቅ ፌስታሎች መጠቀም ችግር እንደሌለው በአንዳንድ አካላት ሲገለፅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ባለስልጣሉ የፕላስቲክ ከረጢትን የሚተኩ ምርቶችን ከሚያመርቱ አካላት ጋር ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ “ምንም አይነት የተፈቀደ የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) የለም” ብለዋል።

ባለስልጣኑ የተኪ ምርቶች በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችል የውይይት መድረክ ከአምራቾች ጋር ባደረገው ውይይት ተኪ ምርት አምራቾች ምርቶችን በስፋት እንዲያመርቱ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንሚያደርግም ጠቁመዋል።

ተኪ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉን የጠቆሙት ኃላፊው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

በመዲናዋ ብክለት ከሚያስከትሉ የፕላስቲክ አይነቶች መካከል የፕላስቲክ ከረጢቶች 46 በመቶውን እንደሚይዙ የገለፀው ባለስልጣኑ የውሃ እና ለስላሳ መጠጥ ጠርሙሶች 34 በመቶ፣ የቤት ዕቃዎች 13 በመቶ እንዲሁም ሌሎች ምርቶች 4 በመቶ የብክለት መጠን እንደሚያስከትሉም ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ዲሪባ፣ አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፕላስቲኮች ላይ የወጣው ህግ በአግባቡ እየተተገበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም የሚከለክል ሕግ ከጥር 23 ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን ይታወሳል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates