ዲፕሎማሲ

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ከኬንያ ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸው ታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/06/2018፡- በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የውኃ ሐብት እና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ስዊላም የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ትናንት የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ኬንያን ጎብኝቷል።

የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኬንያ ዋና የምክር ቤት ፀሐፊ ሙሳሊያ ሙሳቫዲ እና ሌሎችም ከፍተኛ ሹሞች ጋር በቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ አሁናዊ ሁኔታዎች ላይ መወያየተቻውን ካይሮ አስታውቃለች።

የግብፅ ውኃ ሐብት እና መስኖ ሚኒስቴር ንግግሩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ የሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት በቀጣናው በዋናነት ደግሞ በሶማሊያ እና ሱዳን ሰላም እና መረጋጋትን መመለስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሐሳብ መለዋወጣቸው ተጠቁሟል።

ሁለቱ ወገኖች ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር የመከላከያ እና የተቀናጀ የውሃ ሐብት አስተዳደርን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ላይ ለመተባበር ተስማምተዋል።

የናይል ወንዝን ዘላቂነት ለመጠበቅ እና የጋራ ሐብትነቱን ለማስጠበቅ በጥምረት መስራት አስፈላጊ ስለመሆኑ ሁለቱም ወገኞች እውቅና እንደሰጡ ተመላክቷል።

አገራቱ “ሁሉም የናይል ተፋሰስ አገራት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት አድርጎ በውሃ ደኅንነት፣ በማኅበረ ኢኮኖሚ እድገት እና በስነ ምህዳር ጥበቃ በጋራ ለመስራት” ስለማሰባቸው ተጠቅሷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates