ኢኮኖሚኤስያ

ቻይና ከ53 የአፍሪካ ሀገራት ለሚገቡ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ የገበያ ዕድል መፍቀዷን ተገለጸ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/06/2018፡- የቻይና መንግሥት ከሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ53 የአፍሪካ ሀገራት ወደ ሀገሪቱ ገበያ ለሚገቡ ምርቶች ምንም ዓይነት የታሪፍ ክፍያ (ቀረጥ) እንደማያስከፍል አስታወቀ።

ይህ ውሳኔ የሀገሪቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ታስቦ የተወሰነ መሆኑን የቻይና መንግሥት መግለጫን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል።

እንደ መግለጫው ከሆነ፣ ቻይና በኢኮኖሚ ትብብር ላይ ያተኮሩ ስምምነቶችን ከበርካታ አገሮች ጋር ማድረጓን ትቀጥላለች።

በተጨማሪም የዚህ ውሳኔ ዋነኛ ዓላማ “ለአፍሪካውያን የንግድ ገበያን በማስፋፋት ምቹ የንግድ ሥርዓት መፍጠር” እንደሆነ ተገልጿል።

አሜሪካ የአጎዋ ዕድል በምታጠብበትና ከፍተኛ ቀረጥ በምትጥልበት ወቅት ቻይና እንደዚህ ዓይነት ውሳኔ መወሰኗ የዲፕሎሚሲ የበላይነት ለማረጋገጥ ያስችላታል እየተባለ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates