መካከለኛ ምስራቅ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢራን ያበለፀገችውን ዩራኒየም ማስረከብ አለባት አሉ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/06/2018፡- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አሜሪካ ከቴህራን ጋር በምታደርገው ድርድር ያበለፀገችውን ዩራኒየም በሙሉ እንድታስረክብ እና የበለጠ እንዳታበለጽግ ልትታገድ ይገባል አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እሁድ ዕለት በእየሩሳሌም ባደረጉት ንግግር በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በሚካሄደው የኒውክሌር ድርድር ወቅት መኖር ስላለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ዘርዝረዋል።

“ሁሉም የበለፀጉ ዩራኒየሞች ከኢራን መውጣት አለባቸው” ያሉት ኔታንያሁ “ምንም የማበልጸግ አቅም መኖር የለበትም” ሲሉ ተናግረዋል።

ኔታንያሁ ይህንን ያሉት የኢራን እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማክሰኞ በስዊትዘርላንድ ለሚካሄደው ሁለተኛ ዙር ድርድር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ነው።

ኢራን የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ አሜሪካ ማዕቀቦችን የምታነሳ ከሆነ ዝግጁ መሆኗን የኢራኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማጂድ ታክት-ራቫንቺ በቴህራን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢራን፤ አሜሪካ የጣለችባትን ማዕቀቦች ለማንሳት ፈቃደኛ ከሆነች፤ ከአቋሟ ፈቀቅ ብላ የኒውክሌር ስምምነት ላይ የመድረስ ሐሳብን ለማጤን ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ኢራን ምንም ዩራኒየም ማበልጸግ የለባትም የሚለውን እንደ ቀይ መስመር እና በኒውክሌር አለማስፋፋት ስምምነት መሠረት መብቷን መጣስ አድርጋ ትቆጥራለች ብሏል።

አሜሪካ ኢራን ስምምነት ላይ እንድትደርስ ጫና እያደረገች ሲሆን በመካከለኛው ምሥራቅም ያላትን ወታደራዊ አቅም በማጠናከር፣ ሁለት የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችን ወደ ቀጣናው ማስጠጋቷ ይታወሳል።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ዛሬ ጄኔቫ ገብቷል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለሚያደርጉት ሁለተኛው ዙር የኒውክሌር ድርድር የስዊትዘርላንድስ ዋና ከተማ ጄኔቫ ገብቷል።

አሜሪካ እና ኢራን በተዘዋዋሪ የሚያደርጉት ድርድር ማክሰኞ ዕለት በጄኔቫ እንደሚጀመር ተገልጿል። ድርድሩን የምትመራው ኦማን መሆኗ የተገለፀ ሲሆን የአሜሪካ ልዑካን ቡድንን ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጄሬድ ኩሽነር እንደሆኑ ታውቋል።

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዋሺንግተን ውጤታማ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል።

“ከኢራን ጋር ማንም ውጤታማ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻለም፤ እኛ ግን እየሞከረን ነው” ብለዋል። አክለውም “ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጄሬድ ኩሽነር ከኢራን ጋር ለሚደረገው ድርድር ወደ ስፍራው እያመሩ ነው፤ የሚሆነውን እናያለን” ብለዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates