የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በአፍሪካ ከ110 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት እንዳላት አስታወቀች፡፡
ከሰሃራ በታች ባሉት አገራት 19 ኤምባሲዎች በመክፈትም በአፍሪካ ያላት ዲፕማሲያዊ ግንኙነት እያሳደገች እንደሆነች ገልፃለች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/06/2018፡- የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ከአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ በሰጡት የሰጡት መግለጫ ኤሚሬትስ በኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ እንዲሁም በሰብአዊ ድጋፍ ከአፍሪካ ጋር ያላት ዕድገት ዳስሰዋል፡፡
ሚኒስትር ዲኤታው ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን እንዳሉት የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ
ከአፍሪካ ጋር ያላት ታሪካዊ ግንኙነት በንግድ፣ በቀይ ባህር እና በህንድ ውቅያኖስ ኮሪደሮች እንዲሁም በህዝብ ለሕዝብ ያተኮረ ነውብለዋል።
ዛሬ፣ ያ ታሪካዊ ትስስር እየጨመረ በመምጣት በዲፕሎማሲ አሻራ ተንፀባርቀዋል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ከሳሃራ በታች ባሉ ሃገራት ብቻ 19 ኤምባሲዎች መክፈትዋ አረጋግጠዋል፡፡
በኢኮኖሚ ዘርፉ እ.አ.አ. ከ2019 እስከ 2023 ባሉት አምስት ዓመታት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአፍሪካ ከ110 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ፈጽማለች፤ ይህም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከማንኛውም ሀገር በላይ ከፍተኛው ደረጃ እንደሚይዝ አስረድተዋል።
ይህ የኢንቨስትመንት መጠንም ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነው ለኢነርጂ፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ለታዳሽ ዘርፎች የዋለ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአፍሪካ አገሮች ማለትም ናይጄሪያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሴራሊዮን፣ ጋቦን፣ አንጎላ፣ ኬንያ፣ ኮንጎ-ብራዛቪል፣ ሞሪሺየስ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር 9 አጠቃላይ የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነቶችን ማድረግዋም ሚኒስትር ዲኤታው ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ገልፀዋል፡፡
በሎጂስቲክስ ዘርፍ በኩል፣ ዲፒ ወርልድ በአፍሪካ ወደቦች ላይ ስራዎችን ማስፋፋቱን እንደቀጠለ ይህም በታንዛኒያ የዳሬ ሰላም ወደብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማሻሻያ ያካትታል ብለዋል፡፡
የኤዲ ፖርትስ በሉዋንዳ አዲስ ተርሚናል ተገንብተዋል፣ ይህም በአንጎላ ውስጥ የኮንቴይነር አቅምን በእጅጉ መጨመሩ አስረድተዋል፡፡
ኤሚሬትስ ከኢንቨስትመንት ባሻገር፣ በሰብአዊ ተሳትፎም ጉልህ ድርሻ እንዳላት የተገለፀ ሲሆን ባለፉት አስርት ዓመታት፣ ወደ 40 በመቶ የሚሆነው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አጠቃላይ የውጭ እርዳታ ወደ 20.9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚጠጋ ወደ አፍሪካ አገሮች የተላከ ሲሆን ይህም ልማትን፣ ሰብአዊነትን እና የበጎ አድራጎት ድጋፍን እንደሚሸፍን ተገልፀዋል፡፡
አገሪቱ በቀጣይ በየውሃ እና የአየር ንብረት መቋቋም ቅድሚያ የምተሰጣቸው ነገሮች እንደሆኑ በመጥቀስ ከታህሳስ 2-4 ቀን 2026 ከሴኔጋል ጋር የ2026ቱን የተባበሩት መንግስታት የውሃ ኮንፈረንስ በጋራ እንደምታስተናግድ ተገልፀዋል።



