ኢትዮጵያ
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊን ጨምሮ የተለዬዩ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ቀጥላል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/06/2018፡- የአፍሪካ መሪዎች ለ39ኛው የአፍሪካ_ኅብረት ጉባዔ አዲስ አበባ እየገቡ ሲሆኑ የሁለትዮሽ ውይይቶችም እየተካሄዱ ነው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች እና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ በሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ (ዶ/ር)ን፣ ትናንት የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብቷል።
ዋና ጸሐፊው በጉባዔው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከአህጉሪቱ መሪዎች ጋርም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ታውቋል።
የወቅቱ የኅብረቱ ሊቀ መንበር እና የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ እና የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሰላም አብዲ፣ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀሲካ አሊፖ፣ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ፣ የኮትዲቯር ምክትል ፕሬዚዳንት ቲዬሞኮ ሜይሊየት ኮኔ፣ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እና ሌሎች በርካታ መሪዎች ለጉባኤው አዲስ አበባ ገብቷል።



