ፖለቲካ
መራጮች ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን ወደ የካቲት 28 ተራዘመ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/06/2018፡- የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን ወደ የካቲት 28 ቀን 2018 ተራዝሟል አለ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ቦርዱ እያከናወናቸው በሚገኙ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የመራጮች ምዝገባ የካቲት 7 ቀን 2018 እንደሚጀመር ተገልጾ የነበረ ሲሆን፥ ወደ የካቲት 28 ቀን 2018 መራዘሙን ተናግረዋል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፣ ቀደም ሲል የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7 ቀን ለማከናወን ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ቀሪ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ሲባል የምዝገባው መጀመሪያ ቀን ወደ የካቲት 28 እንዲራዘም ተደርጓል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የእጩዎች ምዝገባ ማብቂያ ጊዜም ወደ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ተራዝሟል።



