የተለያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአቶ አማን ፍሥሐ ጽዮን ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/06/2018፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢቢኤስ ቴሌቭዥን መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍሥሐ ጽዮን ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኀዘን መግለጫ መልዕክታቸው፣ “የኢቢኤስ ቴሌቭዥን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍሥሐ ጽዮን በማረፉ ኀዘን ተሰምቶኛል” ብለዋል።
አማን ለኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ዕድገት ወሳኝ ሚና ከነበራቸው አንዱ መሆናቸውን እና ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፈች ጊዜ ሁሉ የሚጠበቅበትን ማድረጋቸውን ገልጸው፣ ፈጣሪ ነፍሱን በሰላም ያሳርፋት ብለዋል።
የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የቴሌቪዥን ጣቢያው ይፋ አድርገዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ሚዲያ ዕድገት ስኬት የማይተካ ሚና የተጫወቱት አቶ አማን፤ የታላቅ ራዕይ ባለቤትና ብርቱ ሰው እንደነበሩም ኢቢኤስ ባወጣው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል።


