ኢራን የምታመርተውን የበለፀገ ዩራኒየም ልትቀንስ እንደምትችል አስታወቀች፡፡
ነገር ግና ይህን የምታደርገው ያቀረበችውን ቅድመ ሁነት የሚሟላላጽ ከሆነ ነው፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/06/2018፡- ኢራን ሁሉም ማዕቀቦች የሚነሱላት ከሆነ የበለጸገ ዩራኒየሟን የጥራት ደረጃ ልትቀንስ እንደምትችል አስታወቀች፡፡
ኢራን የተጣሉባት ማዕቀቦች በሙሉ የሚነሱላት ከሆነ በከፍተኛ መጠን ያበለጸገችውን ዩራኒየም የጥራት ደረጃ ዝቅ ለማድረግ ልትስማማ እንደምትችል የአገሪቱ የአቶሚክ ኃላፊ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘገበዋል።
ኢራን ያቀረበችው ይህ ሐሳብ ከአሜሪካ ጋር እያደረገችው ባለችው ድርድር በግልጽ አቋሟ የተንጸባረቀበት ተደርጎ ተቆጥሯል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የባሕር ኃይላቸውን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ማሰማራቸውን ተከትሎ በዋሽንግተን እና ቴህራን መካከል ጦርነት ይነሳል የሚል ስጋት ተስተውለዋል።
ይህ ስጋት ማየሉን ተከትሎም የአሜሪካ እና ኢራን ዲፕሎማቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦማን አደራዳሪዎች አማካኝነት ኦማን ውስጥ ንግግር ያደረጉ ሲሆን
የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቋም ባለፈው ዓመት ይፋ ያደረገው ግምት እንደሚያሳየው ኢራን ከ400 ኪሎ ግራም በላይ የሆነ ዩራኒየም አከማችታለች። የኢራን ዩራኒየም እስከ 60% የሚደርስ የጥራት ደረጃ እንዳለውም ተገልጿል።
ዩራኒየም ለጦር መሣሪያነት ደረጃ ደርሷል የሚባለው 90% ጥራት ሲኖረው ሲሆን የኢራን ክምችት እዚህ ላይ ለመድረስ አንድ እርምጃ ብቻ የቀረው እንደሆነም ተቋሙ አስታውቋል።
እስካሁን ድረስ ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር በተደረገው ንግግር የኢራንን የበለጸገ ዩራኒየም ወደ ሌላ አገር የመላክ ሐሳብ እንዳልተነሳም ኃላፊው መናገራቸውን የኢራን የዜና ወኪል ዘግቧል።
ቀጣዩ ዙር የአሜሪካ እና ኢራን ድርድር የሚካሄድበት ጊዜ እና ቦታ እስካሁን አልታወቀም።
አሜሪካ ከፍተኛ ጫናዎችን ከማሳደር ከተቆጠበች እና ቃሏን የምታከብር ከሆነ ተፈላጊው ውጤት ላይ መድረስ እንደሚቻልም ተገልጸዋል።



