የተለያዩ
በሞቃዲሾ አየር ማረፊያ መንገዶኞች አሳፍሮ በነበረው አየር አደጋ መከሰተ ተገለፀ፡፡
ሁሉንም ተሳፋሪዎች በአደጋው ሳይጎዱ መውጣት እንደቻሉ ተገልፀዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/06/2018፡- ወደ ጋልካዮ ሲጓዝ የነበረ የሲቪል አውሮፕላን በረራው ከጀመሩ ከ15 ደቂቃ በፊት በሞቃዲሾ አደን አዴ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ አደጋ እንዳጋጠመው ተገለፀዋል።
የአየር ማረፊያ ባለስልጣናት እንደገለጡሉት አውሮፕላኑ ወደ ሞቃዲሾ ለመመለስ ቢሞክርም በማረፍ ሂደቱ ወቅት ከማኮብኮቢያው ወጥቶ ነበር።
አውሮፕላኑ አደጋው በተከሰተበት ወቅት 55 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረ ሲሆን ምንም አይነት ጉዳት ወይም ሞት እንዳልተዘገበ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል።
የአደጋው መነሻ ቴክኒካል ችግር ከመባሉ ውጪ በዝርዝር ተባለ ነገር የለም፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ሶማሊያ የመጀመሪያ የተባለለት የአየር መከላከያ ስርዓት ማግኘትዋ ተገልፀዋል፡፡
ወታደራዊ ምንጮች እንደገለፁት፣ ቱርክ የመጀመሪያውን የአየር መከላከያ ስርዓት ፓኬጅ፣ ፀረ-አውሮፕላን መሳሪያዎችን ጨምሮ፣ ወደ ሞቃዲሾ ማድረስዋ ታውቀዋል፡፡
ትላንት በሶማሊያ ዋና ከተማ የአየር መከላከያ ስርዓቶችን የያዘ የቱርክ አየር ኃይል የጭነት አውሮፕላን ማረፉ ምንጮች በመጥቀስ ጋረዎይ ኦንላይን ዘግበዋል።
የሶማሊያ መንግስት በዚህ እርምጃ የአየር መከላከያ አቅሙን ለማሳደግ እና የሶማሊያ አየር ኃይል አቅምን ለማጠናከር ያለመ ነው እንደሆነም ተገልፀዋል።


