ኢትዮጵያ

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር በቦሌ አየር ማረፊያ የአገራቸውን አምባሳደር ጠርተው አነጋገሩ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/06/2018፡- የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ከማል ኢድሪስ ዛሬ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለጥቂት ደቂቃዎች ቆይታ አድርገዋል፡፡

ይህንን ቆይታ ያደረጉትም ከነበራቸው የውጭ አገር ጉዞ ወደአገራቸው የሚመለሱበትን አውሮፕላን በሚጠባበቁበት ወቅት ነው፡፡

በዚህ ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የሱዳን አምባሳደር ጠርተው አነጋግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቋሚ አምባሳደርና የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ተወካይ የሆኑት አሊ ዘይን ኢብራሂም ወደቦሌ በመሄድ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተወሰነ ውይይት አከናውነዋል፡፡

በዚህ ውይይትም ኤምባሲያቸው ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ እያደረገ ያለውን ዝግጅት ያብራሩ ሲሆን የኢዮጵያና የሱዳንን ግንኙነት ለማጠናከር ኤምባሲው እያደረገው ያለውን እቅድ መግለፃቸውን ሱዳን ሆራይዘን ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ኤምባሲው እያከናወናቸው ላሉት እነዚህ ስራዎች ያላቸውን አድናቆት መግለፃቸውን ዘገባው አስረድቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት በነበረው ስብሰባ ላይ ተሳትፈው ወደአገራቸው እየተመለሱ ነበር፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates