
ኢትዮ ሞኒተር፡ 28/05/2018፡- የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ ረቡዕ ዕለት የብሔራዊ የአደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ የአስቸኳይ ጊዜ ኦፕሬሽን ማዕከልን ከጎበኙ በኋላ ሁሉም የመንግስት ተቋማት ለአስቸኳይ ጊዜ የድርቅ ምላሽ ቅድሚያ እንዲሰጡ አዝዘዋል።
ፕሬዝዳንቱ በጣም በተጎዱ አካባቢዎች፣ መፈናቀሎቸ፣ የአካባቢ መሸርሸር እና የህይወት መጥፋትን ጨምሮ ከኤጀንሲው ባለስልጣናት ዝርዝር መግለጫ ተሰጥቶዋቸዋል።
ባለስልጣናቱ ቀውሱ ወደ አደገኛ ደረጃ መድረሱን እና አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ ረሃብ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝዳንት ሙሃመድ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሶማሊያ የንግድ መሪዎች፣ የሰብአዊ ድርጅቶች እና አለም አቀፍ አጋሮች እየጨመረ የመጣውን የሰብአዊ አደጋ ምላሽ ለመስጠት እና ተጨማሪ የሰው ልጅ ስቃይ ለመከላከል አንድ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
እንዲሁም የሀገሪቱ የፋይናንስ ባለስልጣናት ወደ ሶማሊያ የሚገቡ ከድርቅ እርዳታ ጋር የተያያዙ ሁሉንም እርዳታዎች፣ ልገሳዎች እና አገልግሎቶች ከግብር ነፃ እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጥተዋል፣ ይህም ለተጎዱ ማህበረሰቦች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማፋጠን ያለመ ነው ተብሏል።
ሸበሌ ሬድዮ ያወጣው ይህ መረጃ ምን ያህል ህዝብ በድርቅ እንደተመታ እና ለረሃብ እንደተጋለጠ ያለው ነገር የለም።



