አፍሪካ

የሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ሰጪው እና የሰሜኑ ህዝባዊነፃ አውጪ ንቅናቄ ግንባር ስትራቴጂካዊ ቦታን መቆጣጠራቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 27/05/2018፡- የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች እና የሰሜን ሱዳን ሕዝባዊ ነፃ አውጪ ንቅናቄ ማክሰኞ ዕለት በደቡብ ምስራቅ ሱዳን ብሉ ናይል ክልል በሚገኙ ሦስት ቦታዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ስትራቴጂካዊቷን የዴይም ማንሱር ከተማን መቆጣጠሩ አስታውቋል።

ጥቃቱን ተከትሎ አንድ የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ታጣቂ ኃይሎችን እንድያልፉ እያመቻቸች ነው ሲሉ ከሷል።

በአብደል አዚዝ አል-ሂሉ የሚመራው የሰሜኑ ነፃ አውጪ ንቅናቄ፣ ከሱዳን ጦር ጋር ውጊያዎች ካደረገ በኋላ በኩርሙክ ካውንቲ ውስጥ የዴይም ማንሱርን ስትራቴጂካዊ ከተማ እንዲሁም በኩርሙክ ካውንቲ ውስጥ በባሺር ኑኩ እና ቾር አል-ቡዲን መቆጣጠሩን አስታውቋል።

ንቅናቄው በፌስቡክ ገፁ ባሰራጨው ፅሑፍ በተጠቀሱ ቦታዎች ላይ በፈፀመው ጥቃት የጦር ተሽከርካሪዎችና ታንኮችን መያዙን ገልጿል።

ታማኝ ምንጮች እደገለፁት፣ ውጊያው በድሮን ጥቃቶች የተደገፈ እንደነበር እና የሱዳን ሰራዊት የጦር መሣሪያ ክምችቶች እንደወደሙ ተዘግቧል።

የሱዳን ሰራዊት እስካሁን ስለእነዚህ ክስተቶች ምንም አስተያየት አልሰጠም። ይሁን እንጂ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የRSF እና SPLM-N ኃይሎችን እንድያልፉ እያመቻቸ ነው በማለት ከሷል።

እነዚህ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ሆነው በኩርሙክ ካውንቲ ውስጥ የጦር ሰፈሮችን ለማጥቃት መጀመራቸውን ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ እንዳሉት ከሶስት ቀናት በፊት ከቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የመጡ የ RSF እና የSPLM-N ቡድኖችን ከኢትዮጵያ ሰርጎ ገብተው በሰማያዊ ናይል ክልል በያቡስ አካባቢ ድንበር አቋርጠው መግባታቸውን ወታደራዊ መረጃ ዘግቧል።

በተጨማሪም ማክሰኞ ዕለት በብሉ ናይል ክልል ውስጥ የጦር መከላከያዎችን ለማጥቃት የሚያገለግሉት ድሮኖች በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቁጥጥር ስር ካሉ ሰፈሮች የተነሱ መሆናቸውን አብራርተዋል።

የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ተደጋጋሚ ክስ ቢያቀርብም የኢትዮጵያ መንግስት ግን በግዛቱ የፈቀደው የስልጠና ማእከልና የሚደግፈው ታጣቂ እንደሌለ ደጋግሞ ገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates